عَنْ جَرِيرٍ رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَنْ يُحْرَمِ الرِّفْقَ يُحْرَمِ الْخَيْرَ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2592]
المزيــد ...
ከጀሪር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ለስላሳነትን የተነፈገ ሰው መልካምን ተነፍጓል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2592]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለስላሳነትን የተነፈገ ሰው በዲናዊ፣ በዱንያዊ፣ ለራሱ በሚሰራቸው፣ ከሌሎች ጋርም ባለው ጉዳዮች ለስላሳነትን ያልተገጠመ (ያልታደለ) ሰው በርግጥም መልካምን ሁሉ እንደተነፈገ ተናገሩ።