+ -

عن تميم الداري رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«الدِّينُ النَّصِيحَةُ» قُلْنَا: لِمَنْ؟ قَالَ: «لِلهِ وَلِكِتَابِهِ وَلِرَسُولِهِ وَلِأَئِمَّةِ الْمُسْلِمِينَ وَعَامَّتِهِمْ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 55]
المزيــد ...

ከተሚም አድዳሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፦
"ሃይማኖት (ኢስላም) መቆርቆር (ታማኝነት) ነው።" እኛም "ለማን ነው (የምንቆረቆረው) ታማኝ የምንሆነው?" አልናቸው። እሳቸውም "ለአላህ፣ ለመጽሐፉ፣ ለመልክተኛው፣ ለሙስሊሞች መሪዎችና ለአጠቃላይ ሙስሊም ማህበረሰብ።" አሉ።

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 55]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የኢስላም ሃይማኖት በኢኽላስና በእውነተኝነት ላይ የቆመ መሆኑን ተናገሩ። ይህም ሁሉም አማኝ የታዘዘውን አላህ ግዴታ ባደረገው መልኩ ምንም ሳያጓድልና ሳያታልል በተሟላ መልኩ እስኪፈፅም ድረስ ነው ቅን እንዲሆን የታዘዘው።
ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "ለማን ነው ተቆርቋሪነቱ (ታማኝነቱ)?" ተብለው ተጠየቁ። እሳቸውም እንዲህ አሉ፦
በመጀመሪያ: ጥራት ለተገባውና ከፍ ላለው አላህ ተቆርቋሪ (ታማኝ) መሆን ነው። ይህም፦ ለሱ የምንሰራውን ስራ በማጥራትና ባለማጋራት፣ በጌትነቱ፣ በተመላኪነቱ፣ በስሞቹና በባህሪያቶቹ በማመን፣ ትእዛዞቹን በማላቅና በሱ ወደማመን ሌሎችን በመጣራት ነው።
ሁለተኛ: ለመጽሐፉ ተቆርቋሪ (ታማኝ) መሆን ነው። እሱም የተከበረው ቁርአን ነው። ይህም: ቁርአን የአላህ ቃል መሆኑንና የመጨረሻው መጽሐፉ መሆኑን በማመን፣ ከእሱ በፊት የነበሩትን ሁሉ ድንጋጌዎች የሻረ መሆኑን በማመን፣ እሱን በማላቅ፣ ትክክለኛ በሆነ መልኩ በማንበብ፣ ግልፅ የሆኑትን በመተግበር አሻሚ የሆኑትን በማመን፣ ከአጥማሚዎች ትርጓሜም በመከላከል፣ በተግሳፆቹ በመመከር፣ ውስጡ ያሉትን እውቀቶች በማሰራጨትና ወደርሱ በመጣራት ነው።
ሶስተኛ: ለመልክተኛው ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) መሆን ነው። ይህም: እሳቸው ከመልክተኞች የመጨረሻ መሆናቸውን በማመን፣ ከሳቸው የመጣውን ሁሉ እውነትነቱን በመቀበል፣ ትእዛዛቸውን በመፈፀም፣ ክልከላቸውን በመራቅ፣ እሳቸው ባመጡት ድንጋጌ ካልሆነ በቀር አላህን ባለማምለክ፣ ሐቃቸውን በማላቅና በማክበር፣ ጥሪያቸውን በማሰራጨት፣ ሸሪዐቸውን በማስፋፋት፣ እሳቸው ላይ የሚቀርቡ ክሶችን ውድቅ በማድረግ ነው።
አራተኛ: ለሙስሊም መሪዎች ቅን ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) መሆን ነው። ይህም: በሀቅ ላይ በመተባበር፣ ጉዳያቸውን ባለመጋፋትና በአላህ ትእዛዛቶች ሲያዙን እነሱን ሰምቶ በመታዘዝ ነው ።
አምስተኛ: ለሙስሊሞች ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) መሆን ነው። ይህም: ለነሱ በጎ በማድረግ፣ እነሱን ወደ በጎ በመጣራት፣ እነሱ ላይ ጉዳት ከማድረስ በመቆጠብ፣ ለነሱ መልካምን በመውደድ፣ በበጎና አላህን በመፍራት ላይ ከነርሱ ጋር በመተባበር ነው።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ለሁሉም (ቅን/ ታማኝ) መሆን መታዘዙን እንረዳለን።
  2. በእስልምና ሃይማኖት ውስጥ (ቅን/ ታማኝ) የመሆን ደረጃ የላቀ መሆኑን እንረዳለን።
  3. የእስልምና ሃይማኖት እምነቶችን፣ ንግግሮችንና ተግባራቶችን ያጠቀለለ መሆኑን እንረዳለን።
  4. ከታማኝነት መካከል አንዱ ቅንነቱ ለተገባው አካል ከማታለል ነፍሳችንን ማፅዳትና ለሱ መልካምን መፈለግ ነው።
  5. መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድን ነገር በጥቅሉ አውስተው ከዚያም መዘርዘራቸው የሳቸውን የማስተማር ብቃታቸው ውበትን ይጠቁማል።
  6. ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለአላህ ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) በመሆን ጀምረው ከዚያም ለመጽሐፉ ከዚያም ለመልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከዚያም ለሙስሊም መሪዎች ከዚያም ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) በመሆን ማጠቃለላቸው የትኛውም ነገር እጅግ አንገብጋቢ ከሆነው ጉዳይ ሊጀመር እንደሚገባው እንረዳለን።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري الفولانية Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأكانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ