عن جابر رضي الله عنه قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول:
«أَفْضَلُ الذِّكْرِ: لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، وَأَفْضَلُ الدُّعَاءِ: الْحَمْدُ لِلهِ».

[حسن] - [رواه الترمذي والنسائي في الكبرى وابن ماجه]
المزيــد ...

ጃቢር ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ማለቱ ተላልፏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡
"በላጩ ዚክር 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን በላጩ ዱዓእ ደግሞ 'አልሐምዱሊላህ' ማለት ነው።'"

ሐሰን ነው። - ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በላጩ ዚክር "ላ ኢላሃ ኢለሏህ" - ትርጉሙም፡ ከአሏህ በቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው የለም - መሆኑን፤ ከዱዓእ በላጩ ደግሞ "አልሐምዱሊላህ" - ትርጉሙም፡ ፀጋንም የሚውለው ለተሟላ ውብ መገለጫም የተገባው እርሱ አላህ ብቻ መሆኑን ማመን - እንደሆነ ተናገሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አሏህን በተውሒድ ቃል ማስታወስና በምስጋና ቃል መማፀን ማብዛት መበረታታቱን እንረዳለን።