عن أبي هريرة رضي الله عنه قال:
لَعَنَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ الرَّاشِيَ وَالْمُرْتَشِيَ فِي الْحُكْمِ.

[صحيح] - [رواه الترمذي وأحمد] - [سنن الترمذي: 1336]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በፍርድ አሰጣጥ ዙሪያ ጉቦ ሰጪንም ተቀባይንም ረገሙ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 1336]

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጉቦ በሚሰጥ፣ በሚቀበልና በሚበላ ሰው ላይ ከአላህ እዝነት እንዲርቅና እንዲባረር ዱዓ አደረጉበት።
ከዚህም መካከል ጉቦ ሰጪው ያለአግባብ ወደ ፍላጎቱ ለመዳረስ ሲል ለዳኞች በተሾሙበት ፍርድ እንዲያዘነብሉ (ኢፍትሃዊ እንዲሆኑ) የሚሰጠው ጉቦ እዚህ ውስጥ ይመደባል።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. ጉቦ መስጠት፣ መቀበል፣ አገናኝ መሆንና ተባባሪ መሆን በተሳሳተ ነገር ላይ መተባበር ስለሆነ ክልክል ነው።
  2. የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጉቦ ተቀባይንም ሆነ ሰጪን ስለረገሙ ጉቦ ከትላልቅ ወንጀሎች የሚመደብ ነው።
  3. ጉቦ በዳኝነትና ፍርድ ላይ ከሆነ የተከናወነው በውስጡ አላህ ካወረደው ፍርድ ውጪ በግፍ መፍረድም ስላለው ከባድ ወንጀልና አደገኛ ኃጢአት ይሆናል።
ትርጉሞችን አሳይ
ቋንቋ: الإنجليزية الأوردية الإسبانية ተጨማሪ (61)
ተጨማሪ