+ -

عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الخُدْرِيِّ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِذَا سَمِعْتُمُ النِّدَاءَ، فَقُولُوا مِثْلَ مَا يَقُولُ المُؤَذِّنُ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 611]
المزيــد ...

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"(የአዛንን) ጥሪ በሰማችሁ ጊዜ ሙአዚኑ (አዛን አድራጊው) እንደሚለው በሉ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 611]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙአዚንን በምንሰማ ጊዜ ለርሱ ጥሪ መልስ በመስጠት ላይ አነሳሱ (አበረታቱ)። ምላሹም በየአንዳንዱ አረፍተ ነገር ሙአዚኑ የሚለውን በማለት ነው። ተክቢራው በሚያደርግ ጊዜ እኛም ከርሱ በኋላ ተክቢራ እናደርጋለን፣ ሁለቱን የምስክር ቃላት (ሸሀደተይንን) በሚል ጊዜ እኛም ከርሱ በኋላ እንላለን፣ (ሐይየ ዐለስ-ሶላህና ሐይየ ዐለል ፈላሕ) የሚሉት ሁለቱ አረፍተ ነገሮች ግን ይለያሉ። ከነርሱ በኃላ የምንለው "ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ" (ብልሃትም ሆነ ኃይል ከአላህ ውጪ የለም) ነውና።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية Malagasisht Oromisht Kannadisht الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሐዲሱ ጥቅል መልዕክት ስለሚያስፈርድ አዛን ባዮች ከበዙ የመጀመሪያው ሙአዚን አዛን ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለተኛውንም ሙአዚን አዛን ተከትሎ ለጥሪው መልስ ይሰጣል።
  2. መፀዳጃ ቤት ውስጥ ወይም እየተፀዳዳ እስካልሆነ ድረስ በማንኛውም ሁኔታ ላይ ቢሆን ለሙአዚን ጥሪ መልስ መሰጠት አለበት።
ተጨማሪ