+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّ الدِّينَ يُسْرٌ، وَلَنْ يُشَادَّ الدِّينَ أَحَدٌ إِلَّا غَلَبَهُ، فَسَدِّدُوا وَقَارِبُوا، وَأَبْشِرُوا، وَاسْتَعِينُوا بِالْغَدْوَةِ وَالرَّوْحَةِ وَشَيْءٍ مِنَ الدُّلْجَةِ».

[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 39]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"የእስልምና ሃይማኖት ገር ነው። አንድም ሰው የእስልምናን ሃይማኖት ከመጠን በላይ አያጠብቅም (ሃይማኖቱ) የሚያሸንፈው ቢሆን እንጂ፤ ሚዛናዊ ሁኑ! አቀራርቡ! አብሽሩ! በማለዳ አምልኮ፣ በቀትር አምልኮና በተወሰነ የሌሊት አምልኮ ታገዙ!"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 39]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የእስልምና ሃይማኖት በሁሉም ጉዳዮች በገርነትና በማቅለል ላይ የተገነባ መሆኑን ገለፁ። አለመቻልና አስገዳጅ ምክንያቶች ሲኖሩም ገርነቱ ይጨምራል። በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ከአቅም በላይ መጥለቅና ገራገርነትን መተውም መጨረሻው አለመቻልና ሁሉንም ወይም የተወሰነውን ስራ ማቋረጥ ነው ። ቀጥለውም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወሰን ሳያልፉ ሚዛናዊ በመሆን ላይ አነሳሱ። አንድ ባሪያ ከታዘዘበት ነገር ማጓደል አይኖርበትም፤ የማይችለውንም ለመስራት አይጫንበትም። ሙሉ ለሙሉ መስራት ካቃተው ወደ ሙሉነት ቀረብ አድርጎ መስራት እንደሚገባ ገለፁ።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስራን አሟልቶ መስራት ያቃተው ሰው ብታንስ እንኳ ዘውታሪነቷን ለማስቀጠል የምትሠራ ሥራ ትልቅ ምንዳ እንደምታስገኝ አበሰሩ። አለመቻል በራሱ ድክመት የመጣ እስካልሆነ ድረስ የምንዳ መጉደልን አያስከትልምና።
ዱንያ እውነታዋ ወደ መጪው ዓለም የምንጓዝበት የጉዞና የመሸጋገሪያ ሀገር እንደመሆኗ መጠን ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አምልኮን ነቃ በሚያደርጉ ሶስት ወቅቶች ላይ ዘውትረን በመፈፀም እንድንታገዝ አዘዙ።
የመጀመሪያው: የማለዳ ጉዞ ነው: ይህም በመጀመሪያው የቀን ክፍል በማምለክ ነው። ወቅቱም በፈጅር ሶላትና በፀሐይ መውጣት መካከል አምልኮን መፈፀም ማለት ነው።
ሁለተኛው: ከዝሁር በኋላ የቀትር ጉዞ ነው።
ሶስተኛው: የሌሊቱን ሁሉ ወይም የተወሰነው ክፍል ላይ የሌሊት ጉዞ ነው። የሌሊት ስራ ከቀን ስራ የሚከብድ ስለሆነ "የተወሰነ ከሌሊትም" በማለት የተወሰነውን ሰአት ብቻ እንድናመልክበት አዘዙ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الرومانية Malagasisht Kannadisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የእስልምና ሸሪዓ ገርነትና ቀላልነትን፤ በቸልተኝነትና ወሰን በማለፍ መካከል ሚዛናዊ መሆኑን እንረዳለን።
  2. አንድ ባሪያ በቻለው ልክ ሳይዘናጋ ወይም ከወሰን በላይ ሳያጠብቅ የታዘዘውን መፈፀም አለበት።
  3. አንድ ባሪያ አምልኮ ሲፈፅም የንቃት ወቅቱን መምረጥ እንደሚገባው እንረዳለን። በተለይ እነዚህ ሶስት ወቅቶች አንድ ባሪያ ሰውነቱ ለአምልኮ ነቃ የሚልበት ወቅቶች ናቸው።
  4. ኢብኑ ሐጀር አልዐስቀላኒ እንዲህ ብለዋል: «ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደሆነ ቦታ መሄድ ያለመን አንድ መንገደኛን የሚያናግሩ ነው የመሰሉት። እነዚህ ሶስት ወቅቶች ለመንገደኛ ምርጥ ወቅቶች ናቸው። ስለዚህ እኛም የንቃት ወቅቶችን እንድንሰራባቸው አስገነዘቡ። ምክንያቱም አንድ ተጓዥ ሌሊቱንም ቀኑንም በሙሉ ከተጓዘ ይደክምና ጉዞውን ያቋርጣል። በነዚህ የሚያነቁ በሆኑ ወቅቶች መጓዝ ላይ ከበረታ ግን ያለምንም ችግር በጉዞው ላይ ለመዘውተር ይመቸዋል።»
  5. ኢብኑ ሐጀር እንዲህም ብለዋል: «በዚህ ሐዲሥ ውስጥ ሸሪዓዊ ማግራሪያዎችን መያዝ እንደሚገባ ተጠቁሟል። በተግራራ ቦታ ላይ ከባዱን ግዴታ ነገር መስራት ማካበድ ነው። ለምሳሌ ውሃ መጠቀም ያልቻለና ውሃን መጠቀሙ ጉዳት የሚያደርስበት በሆነ ወቅት ተየሙምን ትቶ ውሃ ቢጠቀም ማለት ነው።»
  6. ኢብኑ ሙኒር እንዲህ ብለዋል: «በዚህ ሐዲሥ ውስጥ ከነቢያት ምልክቶች መካከል አንዱ ተገልጿል። ይህም እኛም ሆንን ከኛ በፊት የነበሩት በእስልምና ውስጥ ወሰን የሚያልፍ ሰው የሆነ ቦታ ላይ ሲያቋርጥ ማየታችን ነው። በዚህ ሐዲሥ የተሟላን አምልኮ ለመስራት መፈለግን መተው አይደለም የተወገዘው። ይህማ የተወደሰ ጉዳይ ነው። ይልቁንም ወደ መሰላቸት የሚያመራ ወሰን ማለፍ ወይም የተሻለን ለመተው ወይም የግዴታ ነገር ወቅቱ እንዲያልፍ የሚያደርግ በሆነ መልኩ ትርፍ ስራዎች ላይ ወሰን ማለፍ ነው የተከለከለው። ለምሳሌ ያህል ሌሊቱን ሙሉ እየሰገድ አድሮ ሱብሒን በህብረት ሳይሰግድ ወይም ፀሀይ እሰወክትወጣበትና የግዴታው ወቅት እስኪያልፍ ድረስ የሚቆይ ሰው ይጠቀሳል።»