+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لَمَّا خَلَقَ اللَّهُ الْجَنَّةَ وَالنَّارَ أَرْسَلَ جِبْرِيلَ عَلَيْهِ السَّلَامُ إِلَى الْجَنَّةِ، فَقَالَ: انْظُرْ إِلَيْهَا وَإِلَى مَا أَعْدَدْتُ لِأَهْلِهَا فِيهَا. فَنَظَرَ إِلَيْهَا فَرَجَعَ، فَقَالَ: وَعِزَّتِكَ لَا يَسْمَعُ بِهَا أَحَدٌ إِلَّا دَخَلَهَا. فَأَمَرَ بِهَا فَحُفَّتْ بِالْمَكَارِهِ، فَقَالَ: اذْهَبْ إِلَيْهَا فَانْظُرْ إِلَيْهَا وَإِلَى مَا أَعْدَدْتُ لِأَهْلِهَا فِيهَا. فَنَظَرَ إِلَيْهَا، فَإِذَا هِيَ قَدْ حُفَّتْ بِالْمَكَارِهِ، فَقَالَ: وَعِزَّتِكَ لَقَدْ خَشِيتُ أَنْ لَا يَدْخُلَهَا أَحَدٌ. قَالَ: اذْهَبْ فَانْظُرْ إِلَى النَّارِ وَإِلَى مَا أَعْدَدْتُ لِأَهْلِهَا فِيهَا. فَنَظَرَ إِلَيْهَا فَإِذَا هِيَ يَرْكَبُ بَعْضُهَا بَعْضًا، فَرَجَعَ فَقَالَ: وَعِزَّتِكَ لَا يَدْخُلُهَا أَحَدٌ. فَأَمَرَ بِهَا فَحُفَّتْ بِالشَّهَوَاتِ، فَقَالَ: ارْجِعْ فَانْظُرْ إِلَيْهَا. فَنَظَرَ إِلَيْهَا فَإِذَا هِيَ قَدْ حُفَّتْ بِالشَّهَوَاتِ، فَرَجَعَ وَقَالَ: وَعِزَّتِكَ لَقَدْ خَشِيتُ أَنْ لَا يَنْجُوَ مِنْهَا أَحَدٌ إِلَّا دَخَلَهَا».

[حسن] - [رواه أبو داود والترمذي والنسائي] - [سنن أبي داود: 4744]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ ጀነትና እሳትን እንደፈጠረ ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም እንዲህ በማለት ወደ ጀነት ላከው። "ወደ ርሷና በውስጧ ለባለቤቶቿ ያዘጋጀሁትን ተመልከት!" ወደ እርሷ ተመልክቶ በመመለስ እንዲህ አለ፦ "በልቅናህ ይሁንብኝ ስለርሷ ማንኛውም ሰው ቢሰማ ከመግባት ወደኋላ የሚል የለም" አላህም በሷ ጉዳይ ትእዛዙን አስተላልፎ (ለነፍስ) በሚከብዱ ነገሮች ተከበበች። በድጋሚ ጂብሪልን "ወደርሷ ሂድና ወደርሷና በውስጧ ለባለቤቶቿ ያዘጋጀሁትን ተመልከት!" አለው። ወደርሷ ተመለከተ፥ ድንገት (ለነፍስ) በሚከብዱ ነገሮች ተከባ ተመለከታት። "በልቅናህ እምላለሁ! በርግጥም ማንም አይገባትም ብዬ ፈራሁ።" ብሎ ለአላህ መለሰ። አላህም፦ " ወደ እሳትና ለባለቤቶቿ በውስጧ ያዘጋጀሁትን ሂድና ተመልከት" በማለት አዘዘው። ጂብሪልም ወደርሷ ሲመለከት ያንጊዜ እሷ ከፊሏ ከፊሉን ሲበላ ተመለከተ። በመመለስም እንዲህ አለ "በልቅናህ እምላለሁ ማንም አይገባትም" አላህም በሷ ጉዳይ ለስሜት በሚያስደስቱ ነገሮች እንድትከበብ አዘዘ። ቀጥሎም ደግመህ ወደርሷ ሂድና ተመልከት አለው ድንገት ለስሜት በሚያስደስቱ ነገሮች ተከባ ወደርሷ ተመለከተ። "በልቅናህ እምላለሁ! ወደርሷ አንድም ከሷ አይድንም ይገባታል ብዬ ፈራሁ።"

[ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 4744]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አላህ ጀነትና እሳትን እነደፈጠራቸው ለጂብሪል ዐለይሂ ሰላም እንዲህ እንዳለ ተናገሩ። "ወደጀነት ሂድና ወደርሷ ተመልከት!" ጂብሪልም ሄዶ ወደርሷ ተመልክቶ ተመለሰ። ጂብሪልም እንዲህ አለ:- "ጌታዬ ሆይ በልቅናህ እምላለሁ! በውስጧ ስለሚገኘው ፀጋ፣ መከበሪያና መልካም ነገሮች ማንም ቢሰማ ወደርሷ መግባት የሚወድና ስለርሷም ከመስራት አይታቀብም።" በማለት መለሰ። ከዚያም አላህ ጀነትን ለነፍስ የሚከብዱና አስቸጋሪ በሆኑ ትእዛዛቶችን መፈፀምና ክልከላዎችን መራቅ ከበባት። ይህም ወደ ጀነት መግባት የፈለገ ይህን አስቸጋሪ መንገድ ማለፍ እንዲጠበቅበት ነው። ከዚያም የተከበረውና የላቀው አላህ ለነፍስ በሚከብዱ ነገሮች ከከበባት በኋላ እንዲህ አለ፦ " ጂብሪል ሆይ! ወደ ጀነት ሂድና ተመልከታት!" ሄዶ ወደርሷ ተመልክቶ በመምጣት እንዲህ አለ፦ " ጌታዬ ሆይ በልቅናህ እምላለሁ! ወደርሷ በሚያደርገው ጉዞ በሚያጋጥሙት ችግሮችና መከራዎች ምክንያት ማንም አይገባትም ብዬ እፈራለሁ።" አላህ እሳትን የፈጠረ ጊዜ፦ "ጂብሪል ሆይ! ሂድና ወደርሷ ተመልከት" አለው። ወደርሷ ሂዶም ተመለከተ። ከዚያም በመምጣት እንዲህ አለ፦ "ጌታዬ ሆይ በልቅናህ እምላለሁ! ውስጧ ስላለው ቅጣትና ጭንቀቶች አንድም አይሰማም ውስጧ መግባትን በመጥላት ወደርሷ ከሚያስገቡ ምክንያቶችም የራቀ ቢሆን እንጂ።" ከዚያም የተከበረውና የላቀው አላህ እሳትን ከበባት፤ ወደርሷ መድረሻ መንገድንም ለነፍስ የሚያስደስትና የሚያረካትን ነገሮች አደረገ። ከዚያም "ጂብሪል ሆይ! ሂድና ወደርሷ ተመልከት " አለው። ጂብሪልም ወደርሷ ሂዶ ተመልክቶ በመምጣት እንዲህ አለ፦ " ጌታዬ ሆይ በልቅናህ እምላለሁ! በዙሪያዋ ባሉት ለነፍስ አርኪና አስደሳች ነገሮች ምክንያት በርግጥም ከሷ አንድም አይድንም ብዬ ሰጋሁ፤ ፈራሁ።"

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ጀነትና እሳት አሁን ላይ ያሉ መሆናቸውን ማመን እንደሚገባ፤
  2. በሩቅ ምስጢር ነገሮች እና ከአላህና መልክተኛው የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመጡ ነገሮች ሁሉ ማመን ግዴታ መሆኑን፤
  3. ወደጀነት የምታደርስ መንገድ ስለሆነች በአስቸጋሪ ነገሮች ላይ መታገስ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን፤
  4. ወደ እሳት የሚያደርስ መንገድ ስለሆነ ክልክል ነገሮችን መራቅ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን፤
  5. ጀነት በአስቸጋሪ ነገሮች እሳት ደግሞ ለስሜት በሚያስደስቱ ነገሮች የተከበቡ መደረጋቸው በዱንያ ህይወት ውስጥ ፈተናዎችና ሙከራዎች እንዳሉ የሚያሲዝ ነው።
  6. የጀነት መንገድ አስቸጋሪና ከባድ ስለሆነ ትእግስትና ከኢማን ጋር ትኩረት ይፈልጋል። የእሳት መንገድ በዱንያ ውስጥ ለነፍስ በሚያስደስትና በሚያረካ ነገሮች የተሞላ መሆኑን እንረዳለን።
ተጨማሪ