+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه أَنَّهُ سَمِعَ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«أَرَأَيْتُمْ لَوْ أَنَّ نَهَرًا بِبَابِ أَحَدِكُمْ يَغْتَسِلُ فِيهِ كُلَّ يَوْمٍ خَمْسًا، مَا تَقُولُ ذَلِكَ يُبْقِي مِنْ دَرَنِهِ؟» قَالُوا: لَا يُبْقِي مِنْ دَرَنِهِ شَيْئًا، قَالَ: «فَذَلِكَ مِثْلُ الصَّلَوَاتِ الخَمْسِ، يَمْحُو اللَّهُ بِهِ الخَطَايَا».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 528]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ አሉ፦
"'ንገሩኝ እስኪ! አንዳችሁ በር ላይ በየቀኑ አምስት ጊዜ የሚታጠብበት ወንዝ ቢኖር ይህ ከእድፉ ያስቀራል ትላላችሁን?' ሶሐቦችም 'ከእድፉ አንዳችም አያስቀርም።' አሉ። እርሳቸውም 'ይህ የአምስቱ ሶላቶች ምሳሌ ነው። አላህ በሶላት ወንጀሎችን ያብሳል።' አሉ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 528]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በጧትም በማታም የሚሰገዱትን አምስቱ ሶላቶች ትናንሽ ወንጀሎችንና ኃጢአቶችን ማስማራቸውና ማስወገዳቸውን፤ አንድ ሰው በየቀኑ አምስት ጊዜ የሚታጠብበት በሆነ በሩ ላይ እንዳለ ወንዝ መሰሉት። ከእድፉና ቆሻሻው አንዳችም አይቀርምና።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ይህ ትሩፋት ትናንሽ ወንጀሎችን ብቻ በማስማር የተገደበ ነው። ትላልቅ ወንጀሎች የግድ ተውበት ያስፈልጋቸዋል።
  2. አምስቱን ሶላቶች የመፈፀምና የእነርሱን መስፈርቶች፣ ማእዘናቶች፣ ግዴታዎችና ሱናዎችን የመጠባበቅን ትሩፋት እንረዳለን።