عَنِ النُّعْمَانِ بْنِ بَشِيرٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَثَلُ الْمُؤْمِنِينَ فِي تَوَادِّهِمْ وَتَرَاحُمِهِمْ وَتَعَاطُفِهِمْ مَثَلُ الْجَسَدِ، إِذَا اشْتَكَى مِنْهُ عُضْوٌ تَدَاعَى لَهُ سَائِرُ الْجَسَدِ بِالسَّهَرِ وَالْحُمَّى».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከኑዕማን ቢን በሺር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"የአማኞች እርስ በርስ የመዋደዳቸው፣ የመተዛዘናቸውና የመራራታቸው ምሳሌ እንደ አንድ የሰውነት ክፍል ነው። ከርሱ አንድ አካል የታመመ ጊዜ የተቀረው ሰውነት በእንቅልፍ እጦትና ትኩሳት ይሰቃያል።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመውደድ፣ ከማዘን፣ ከመርዳት፣ ከማገዝና እነርሱ ላይ በሚደርስ ጉዳት አብሮ ከመጎዳት አንፃር ሙስሊሞች ከፊሉ ለከፊሉ ሊኖረው የሚገባውን ሁኔታ ልክ እንደ አንድ ሰውነት ምሳሌ ሊሆን እንደሚገባው ግዴታነቱን ገለፁ። አንድ አካል የታመመ ጊዜ የተቀረው አካል በእንቅልፍ እጦትና ትኩሳት አብሮት ይሰቃያል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሙስሊሞችን ሐቅ ማላቅ፤ እነርሱን በማገዝና ከፊሉ ለከፊሉ ማዘን ላይ ማነሳሳት ይገባል።
  2. በእምነት ባለቤቶች መካከል መዋደድና መረዳዳት ሊኖር ይገባል።
ተጨማሪ