+ -

عَنْ مَعْقِلِ بْنِ يَسَارٍ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«الْعِبَادَةُ فِي الْهَرْجِ كَهِجْرَةٍ إِلَيَّ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2948]
المزيــد ...

ከመዕቂል ቢን የሳር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ(የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"በፈተና ወቅት አላህን ማምለክ ወደኔ እንደመሰደድ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2948]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በፈተና፣ በጦርነት፣ የሰዎች ጉዳይ ውጥንቅጡ በወጣ ወቅት አምልኮ ላይ መትጋትን ጠቆሙ። በዚህ ወቅት አምልኮ የማድረግ ምንዳም ወደ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ስደት እንደማድረግ መሆኑንም ተናገሩ። ይህም የሆነበት ሰዎች ከአምልኮ የሚዘናጉበትና ጥቂቶች ካልሆኑ በቀር አምልኮ ላይ የማይሳተፉበት ወቅት ስለሆነ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በፈተና ቀናት ከፈተናው ለመጠበቅና ከብክለት ለመዳን አምልኮ በማድረግና ወደ አላህ በመዞር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. በፈተናና በዝንጉነት ወቅት የአምልኮ ትሩፋት መገለፁ።
  3. አንድ ሙስሊም የፈተናና የዝንጉነት ስፍራዎችን መራቅ እንደሚገባው ያስረዳናል።