+ -

عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«‌إِنَّ ‌أَثْقَلَ صَلَاةٍ عَلَى الْمُنَافِقِينَ صَلَاةُ الْعِشَاءِ وَصَلَاةُ الْفَجْرِ، وَلَوْ يَعْلَمُونَ مَا فِيهِمَا لَأَتَوْهُمَا وَلَوْ حَبْوًا، وَلَقَدْ هَمَمْتُ أَنْ آمُرَ بِالصَّلَاةِ فَتُقَامَ، ثُمَّ آمُرَ رَجُلًا فَيُصَلِّيَ بِالنَّاسِ، ثُمَّ أَنْطَلِقَ مَعِي بِرِجَالٍ مَعَهُمْ حُزَمٌ مِنْ حَطَبٍ إِلَى قَوْمٍ لَا يَشْهَدُونَ الصَّلَاةَ، فَأُحَرِّقَ عَلَيْهِمْ بُيُوتَهُمْ بِالنَّارِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 651]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ፦
"በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባዱ ሶላት የዒሻእ ሶላትና የፈጅር ሶላት ናቸው። በውስጧ ያለውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን ይመጡ ነበር። በርግጥ ሶላት እንዲሰገድ አዝዤ፤ ሰዎችን እንዲያሰግድም አንድ ሰው ላዝ፤ ከዚያም ሶላትን በመስጂድ ተገኝተው ወደማይሰግዱ ሰዎች ቤት የታሰረ እንጨት ከያዙ ወንዶች ጋር በመሄድ በነሱ ላይ ቤቶቻቸውን በእሳት ላቃጥል አስቤም ነበር።'"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 651]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለሙናፊቆችና ሶላት መገኘት ላይ በተለይ የዒሻእና ፈጅር ሶላት ላይ ስላላቸው ስንፍና፤ እነርሱ ሁለቱን ሶላት ከሙስሊም ጀመዓ ጋር መስገድ የሚያስገኘውን አጅር እና ምንዳ መጠን ቢያውቁ ኖሮ ህፃን ልጅ በሁለት እጆቹና ጉልበቱ እንደሚዳኸው እንሱም እየዳኹ ይመጡ እንደነበር ተናገሩ።
_ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ኢቃም እንድትባል አዘው በሳቸው ምትክ አንድ የሚያሰግድ ሰው ሊመድቡና ከዚያም የታሰረ እንጨት ከተሸከሙ ሰዎች ጋር በመሆን ጀመዓ ሶላት ወደማይገኙ ወንዶች ሂደው ጀመዓ ባለመገኘት የሰሩት ወንጀል ከባድ ስለሆነ ቤታቸውን በእሳት ሊያቃጥሉ ቆርጠው ነበር። ነገር ግን ቤት ውስጥ ንፁህ ሴቶች፣ ህፃናትና ሌሎችም የሚያስቀር ምክንያት ያላቸው ስላሉ አላደረጉትም።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht Azerisht الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሶላተል ጀመዓን በመስጊድ ከመስገድ የመራቅ አደገኝነትን እንረዳለን።
  2. ሙናፊቆች በአምልኳቸው ይዩልኝና ይስሙልኝ በስተቀር ሌላ ምንም አያስቡም። ሰዎች በሚያያቸው ጊዜ ካልሆነ በቀር ወደ ሶላት አይመጡም።
  3. ከጀመዓ ጋር ዒሻና ፈጅርን የመስገድ ምንዳ ትልቅነቱን እንረዳለን። እየዳኹ እንኳ ቢሆን ወደነሱ መምጣት የተገባ ነው።
  4. ዒሻና ፈጅር በመስገድ ላይ መጠባበቅ ከንፍቅና መንፃት መሆኑን ከነርሱ መቅረት ደግሞ የሙናፊቆች ባህሪ መሆኑን እንረዳለን።
ተጨማሪ