+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِذَا تَوَضَّأَ أَحَدُكُمْ فَلْيَجْعَلْ فِي أَنْفِهِ ثُمَّ لِيَنْثُرْ، وَمَنِ اسْتَجْمَرَ فَلْيُوتِرْ، وَإِذَا اسْتَيْقَظَ أَحَدُكُمْ مِنْ نَوْمِهِ فَلْيَغْسِلْ يَدَهُ قَبْلَ أَنْ يُدْخِلَهَا فِي وَضُوئِهِ، فَإِنَّ أَحَدَكُمْ لاَ يَدْرِي أَيْنَ بَاتَتْ يَدُهُ». ولفظ مسلم: «إِذَا اسْتَيْقَظَ أَحَدُكُمْ مِنْ نَوْمِهِ فَلَا يَغْمِسْ يَدَهُ فِي الْإِنَاءِ حَتَّى يَغْسِلَهَا ثَلَاثًا، فَإِنَّهُ لَا يَدْرِي أَيْنَ بَاتَتْ يَدُهُ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 162]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"አንዳችሁ ዉዱእ ባደረገ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሀ አድርጎ ከዚያም ያውጣው፣ በድንጋይ ያደራረቀ ሰውም (የድንጋዩን ቁጥር) ጎዶሎ ያድርገው። አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ እጁን ወደ ዉዱእ እቃ ውስጥ ከመክተቱ በፊት እጁን ይጠብ! አንዳችሁ እጁ የት እንዳደረች አያውቅምና።" የሙስሊም ዘገባ ላይ ደግሞ "አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ እጁን ሶስት ጊዜ ከማጠቡ በፊት ወደ እቃ ውስጥ አይንከረው! እርሱ እጁ የት እንዳደረች አያውቅምና።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 162]

ትንታኔ

ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንዳንድ የጠሀራ ህግጋትን ገለፁ። ከነርሱም ውስጥ: የመጀመሪያው: ዉዱእ ያደረገ ሰው ውሀን ወደ አፍንጫው ውስጥ ስቦ ማስገባትና ድጋሚ ከአፍንጫው ማስወጣት ይገባዋል። ሁለተኛው: ሽንት ቤት ውስጥ ከርሱ የሚወጣውን ቆሻሻ ከውሃ ውጪ በድንጋይና በመሳሰሉ ነገሮች ማንፃትና ማስወገድ የፈለገ ሰው የመፀዳጃው ብዛት በጎዶሎ ቁጥር መሆን እንደሚገባ፤ ቢያንስ ሶስት ሲሆን ከፍተኛው ከርሱ የሚወጣውን ቆሻሻ የሚቆርጥና ቦታውን የሚያፀዳለት ያህል ነው። ሶስተኛው: ከሌሊት እንቅልፍ የነቃ ሰው እጁ የት እንዳደረች አያውቅምና ነጃሳ አለመንካቱን ስለማይተማመን እንዲሁም ለሰው ልጅ የሚጎዳ ወይም ውሃውን የሚያበላሽ ነገርን ሰይጣን ወደ እጁ ተሸክሞ አምጥቶ ተጫውቶበት ሊሆንም ስለሚችል እጁን ከእቃው ውጪ ሶስት ጊዜ ሳያጥብ ዉዱእ ለማድረግም መዳፉን እቃ ውስጥ መክተት አይገባውም።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ዉዱእ ላይ ውሃን ወደ አፍንጫ መክተት ግዴታ ነው። እርሱም: ውሃን በትንፋሽ አማካኝነት ወደ አፍንጫ ውስጥ መክተት ሲሆን ልክ እንደዚሁ ውሃውን በትንፋሽ አማካኝነት ከአፍንጫው ማውጣትም ግዴታ ነው።
  2. በጎዶሎ ቁጥር ማደራረቅ እንደሚወደድ እንረዳለን።
  3. ከሌሊት እንቅልፍ በኋላ ሶስት ጊዜ ሁለት እጆችን ማጠብ እንደተደነገገ እንረዳለን።
ተጨማሪ