+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى تَطْلُعَ الشَّمْسُ مِنْ مَغْرِبِهَا، فَإِذَا طَلَعَتْ فَرَآهَا النَّاسُ آمَنُوا أَجْمَعُونَ، فَذَلِكَ حِينَ: {لاَ يَنْفَعُ نَفْسًا إِيمَانُهَا لَمْ تَكُنْ آمَنَتْ مِنْ قَبْلُ، أَوْ كَسَبَتْ فِي إِيمَانِهَا خَيْرًا} [الأنعام: 158] وَلَتَقُومَنَّ السَّاعَةُ وَقَدْ نَشَرَ الرَّجُلاَنِ ثَوْبَهُمَا بَيْنَهُمَا فَلاَ يَتَبَايَعَانِهِ، وَلاَ يَطْوِيَانِهِ، وَلَتَقُومَنَّ السَّاعَةُ وَقَدِ انْصَرَفَ الرَّجُلُ بِلَبَنِ لِقْحَتِهِ فَلاَ يَطْعَمُهُ، وَلَتَقُومَنَّ السَّاعَةُ وَهُوَ يَلِيطُ حَوْضَهُ فَلاَ يَسْقِي فِيهِ، وَلَتَقُومَنَّ السَّاعَةُ وَقَدْ رَفَعَ أَحَدُكُمْ أُكْلَتَهُ إِلَى فِيهِ فَلاَ يَطْعَمُهَا».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 6506]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"ፀሀይ በመግቢያዋ እስክትወጣ ድረስ ሰዓቲቱ አትቆምም። ከመግቢያዋ የወጣችና ሰዎች የተመለከቷት ጊዜ ሁሉም ያምናሉ። ይህም {ከዚህ በፊት አማኝ ያልሆነችን ነፍስ እምነትዋ ወይም በእምነትዋ (ጊዜ) በጎ ያልሠራችን (ነፍስ ጸጸትዋ) አይጠቅማትም።} [አል አንዓም: 158] የተባለበት ወቅት ነው። ሰዓቲቱ ሁለት ሰዎች ሊገበያዩ ልብሶቻቸውን ዘርግተው ሳይገበያዩም ሳይሰበስቡትምም (ድንገት) ትከሰታለች፤ ሰዓቲቱ ሰውዬው ያለበውን ወተት (ለመጠጣት) እንደዞረ ሳይጠጣው (ድንገት) ትከሰታለች፤ ሰዓቲቱ ሰውዬው ምንጩን እያስተካከለ ከሱ ሳይጠጣ (ድንገት) ትከሰታለች፤ ሰዓቲቱ አንዳችሁ ጉርሻውን ወደ አፉ አስጠግቶ ሳይበላት (ድንገት) ትከሰታለች።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6506]

ትንታኔ

የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ከትላልቆቹ የቂያማ ምልክቶች መካከል አንዱ የሆነውን ፀሀይ ከምስራቅ መውጣቷን ቀይራ ከምዕራብ እንደምትወጣ ተናገሩ። ሰዎች በሚያዩዋት ጊዜም ሁሉም ያምናሉ። በዚህ ጊዜ ግን ለከሀዲ ኢማኑ አይጠቅመውም፣ መልካም ሥራም ሆነ ተውበትም አይጠቅመውም። ቀጥለው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሰዎች በዕለትተለት ሁኔታቸውና የህይወት ጉዳያቸው ላይ ሳሉ ቂያማ ድንገት እንደምትመጣ ተናገሩ። ሰዓቲቱ ሻጭና ገዢ ልብሶቻቸውን ለመለዋወጥ ዘርግተው ሳይሻሻጡም ሳይጠቀልሉትም ትከሰታለች። ሰዓቲቱ ሰውዬው የታለበ የግመል ወተቱን ይዞ ሳይጠጣው ትከሰታለች። ሰዓቲቱ ሰውዬው ምንጩን እያስተካከለ በጭቃ እያበጀው ምንም ሳይጠጣ ከሱ ትከሰታለች። ሰዓቲቱ ሰውዬው ወደ አፉ ጉርሻውን ሊበላ እንዳነሳው ሳይበላው ትከሰታለች።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. እስልምናና ተውበት ፀሀይ ከመግቢያዋ እስካልወጣች ድረስ ተቀባይነት አላቸው።
  2. ለሰዓቲቱ በኢማንና መልካም ሥራ መዘጋጀት እንደሚገባ መነሳሳቱ ምክንያቱም ሰዓቲቱ በድንገት ስለምትከሰት።