+ -

عَنْ عُبَادَةَ بْنِ الصَّامِتِ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لَا صَلَاةَ لِمَنْ لَمْ يَقْرَأْ بِفَاتِحَةِ الكِتَابِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 756]
المزيــد ...

ከዑባዳህ ቢን ሷሚት (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"የመጽሐፉን መክፈቻ (ፋቲሓን) ያላነበበ ሰው ሶላት የለውም።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 756]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የፋቲሓን ምዕራፍ በመቅራት ካልሆነ በቀር ሶላት ትክክለኛ እንደማትሆን ገለፁ። ፋቲሓ በሁሉም ረከዓዎች ከሚደረጉ የሶላት ማእዘናት መካከል አንዷ ናት።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ፋቲሓን መቅራት እየቻለ ፋቲሓን ከመቅራት ፋንታ ሌላ ምእራፍ መቅራት አያብቃቃም።
  2. አውቆም ሆነ ሳያውቅ ወይም ረስቶ ፋቲሓ ያልተቀራበት ረከዓ የተበላሸ መሆኑን እንረዳለን። ምክንያቱም ፋቲሓ የሶላት ማእዘን ናት። ማእዘን ደግሞ በማንኛውም ሁኔታ ላይ ቢሆን አይወድቅም።
  3. ተከታይ የሆነ ሰው ኢማሙን ሩኩዕ ላይ ቢደርስበት ፋቲሓን የመቅራት ግዴታው ይነሳለታል።