عَنْ سَعْدِ بْنِ أَبِي وَقَّاصٍ رضي الله عنه عَنْ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنَّهُ قَالَ:
«مَنْ قَالَ حِينَ يَسْمَعُ الْمُؤَذِّنَ أَشْهَدُ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُهُ وَرَسُولُهُ، رَضِيتُ بِاللهِ رَبًّا وَبِمُحَمَّدٍ رَسُولًا، وَبِالْإِسْلَامِ دِينًا، غُفِرَ لَهُ ذَنْبُهُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 386]
المزيــد ...
ከሰዕድ ቢን አቢ ወቃስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"አዛን ሲባል የሰማ ጊዜ: 'አሽሃዱ አን ላኢላሃ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ ወአነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ ረዲቱ ቢላሂ ረበን ወቢሙሐመደን ረሱለን ወቢል ኢስላሚ ዲና' ያለ ሰው ወንጀሉ ይማራል።" (ትርጉሙም: ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም። ብቸኛና አጋር የሌለው ነው። ሙሐመድም የአላህ ባሪያውና መልክተኛው ናቸው ብዬ እመሰክራለሁ፤ በአላህ ጌትነት፣ በሙሐመድ መልክተኝነት፣ በኢስላም ሃይማኖትነት ወድጃለሁ።)
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 386]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: አዛን አድራጊውን የሰማ ጊዜ እንዲህ ያለ ሰው: "አሽሃዱ አን ላኢላሃ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ" ማለትም: ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለና ከርሱ ውጪ የሚመለኩ ሁሉ ከንቱ እንደሆኑ አረጋግጣለሁ፣ አውቃለሁ፣ እናገራለሁ። "ወአነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ" ማለትም: እርሳቸው ባሪያ ናቸውና አይመለኩም፣ መልክተኛ ናቸውና አይስተባበሉም። "ረዲቱ ቢላሂ ረበን" ማለትም: በአላህ ጌትነት፣ ተመላኪነትና በስሞቹና በባህሪያቱ ወድጃለሁ። ማለት ነው። "ወቢሙሐመደን ረሱላ" ማለትም ረሱል በተላኩበት ነገር ሁሉና ባደረሱን ነገር ወድጃለሁ። ማለት ነው። "በእስልምናም" ማለትም: ትእዛዛትም ሆኑ ክልከላዎች በሁሉም የኢስላም ህግጋት "ዲና" ማለትም በማመንና በመመራት ወድጃለሁ። ማለት ነው። "ወንጀሉ ይማራል።" ማለትም ትናንሽ ወንጀሎቹን ይማሩለታል።