1. ዋና ገጽ
  2. ምድቦች
  3. ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ሐዲሥ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለኡዱሒያ ሁለት ቡራቡሬና ቀንዳም የሆኑ ሙክቶችን በእጃቸው አረዱ። "ቢስሚላህ አላሁ አክበር" አሉና እግራቸውን አንገቱ ላይ አድርገው አረዱት።

عَنْ أَنَسٍ رَضيَ اللهُ عنهُ قَالَ:
ضَحَّى النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ بِكَبْشَيْنِ أَمْلَحَيْنِ أَقْرَنَيْنِ، ذَبَحَهُمَا بِيَدِهِ، وَسَمَّى وَكَبَّرَ، وَوَضَعَ رِجْلَهُ عَلَى صِفَاحِهِمَا.

ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል:
«ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለኡዱሒያ ሁለት ቡራቡሬና ቀንዳም የሆኑ ሙክቶችን በእጃቸው አረዱ። "ቢስሚላህ አላሁ አክበር" አሉና እግራቸውን አንገቱ ላይ አድርገው አረዱት።»

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5565

ማብራሪያ

አነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የዒድ አልአድሓ ቀን በእጃቸው ሁለት ቀንዳሞችና ጥቁር የተቀላቀለባቸው ነጫጭ ወንድ ሙክት በጎችን "ቢስሚላህ አላሁ አክበር" በማለት እግራቸውን አንገታቸው ላይ አድርገው እንዳረዱ ተናገረ።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. ኡዱሒያ የተደነገገ እንደሆነ እንረዳለን። በዚህም ጉዳይ ዑለሞች ባጠቃላይ ተስማምተዋል።
  2. ኡዱሒያው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያረዱት አይነት መሆኑ በላጭ ነው። ይህም ሲታይ ስለሚያምርና ሞራውና ስጋውም ጣፋጭ ስለሚሆን ነው።
  3. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: «በዚህ ሐዲሥ መሰረት አንድ ሰው ኡዱሒያውን በራሱ ማረድ እንደሚገባውና በቂ ምክንያት ሳይኖረው ለማረድ ሰው መወከል እንደሌለበት እንረዳለን። በቂ ምክንያት ካለው ግን ሲታረድ መገኘቱ ይወደድለታል። በርሱ ፋንታ እንዲያርድለት ሙስሊም ሰው ከተካ ያለምንም ልዩነት ይፈቀዳል።
  4. ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "በዚህ ሐዲሥ ውስጥ በማረድ ወቅት ቢስሚላህ ከማለት ጋር አላሁ አክበር ማለት እንደሚወደድ፤ እግርን ደሞ በሚታረደው ቀኝ የአንገቱ ክፍል ላይ ማኖር እንደሚወደድ እንረዳለን። የሚታረደውን የምናስተኛው በግራ ጎኑ በመሆኑ ዑለሞች ተስማምተዋል። ለአራጁ ቢላን በቀኝ እጅ መያዝ፣ በግራ እጁ ደግሞ ጭንቅላቱን መያዝ እንዲቀለው እግሩን በሚታረደው እንስሳ ቀኝ አንገት ላይ ያደርጋል።"
  5. ለኡዱሒያ ቀንዳሙን ማረድ እንደሚወደድ እንረዳለን። ቀንድ ከሌለውም ግን ይፈቀዳል።

ትርጉሞችን አሳይ

53 ቋንቋ
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
CS Čeština التشيكية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
AZ Azərbaycan الأذربيجانية
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية