+ -

عَنْ أَنَسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قالَ:
«لاَ يُؤْمِنُ أَحَدُكُمْ، حَتَّى يُحِبَّ لِأَخِيهِ مَا يُحِبُّ لِنَفْسِهِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 13]
المزيــد ...

ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"አንዳችሁ ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 13]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለነፍሱ የሚወደውን አምልኮዎችና ሃይማኖታዊም ይሁን ዱንያዊ መልካም ነገሮችን ለወንድሙ እስከሚወድ ድረስ፤ ለነፍሱ የሚጠላውንም ለርሱ እስኪጠላ ድረስ ለአንድ ሙስሊም የተሟላ ኢማን እንደማይረጋገጥ ገለፁ። በሙስሊም ወንድሙ ላይ የዲን ጉድለት ከተመለከተም ለማስተካከል ይታገላል። በርሱ ላይ መልካምን ከተመለከተም ያበረታዋል፣ ያግዘዋል፣ የዲኑን ወይም የዱንያውን ጉዳይም ይመክረዋል።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አንድ ሙስሊም ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ የመውደድ ግዴታ እንዳለበት እንረዳለን። ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ የማይወድ ሰው ከርሱ ላይ ኢማን ውድቅ መደረጉ ይህን መተግበር ግዴታ መሆኑን ይጠቁማል።
  2. ለአላህ ብሎ ወንድማማች መሆን ከዘር ወንድማማችነትም በላይ ነው። የኢስላማዊ ወንድማማችነት ግዴታውም የበለጠ ነው።
  3. ይህንን ውዴታ የሚቃረን ሁሉ ማጭበርበር፣ ሀሜት፣ ምቀኝነት፣ በሙስሊም ነፍስ ላይ ወይም ገንዘቡ ላይ ወይም ክብሩ ላይ ጠላት መሆንን የመሳሰሉ ንግግርም ሆነ ተግባርም ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
  4. "ለወንድሙ" ከሚለው ቃል እንደምንረዳው ለአንድ ተግባር የሚያነሳሳ የሆነን ቃል መጠቀም ተገቢ እንደሆነ ነው።
  5. ኪርማኒ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል: «ከዚህም በተጨማሪ ለነፍሱ የሚጠላውን መጥፎ ነገር ለወንድሙ መጥላቱም የኢማን ክፍል ነው። ሐዲሡ ላይ ያልጠቀሱት አንድን ነገር መውደድ ተቃራኒውን መጥላት የሚያስፈርድ ስለሆነ በዚህ በመብቃቃት ነው መጥቀሱን የተዉት።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الليتوانية الصربية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht Kannadisht الولوف Azerisht الأوكرانية الجورجية المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ