+ -

عَنْ جَابِرٍ رضي الله عنه قَالَ: سَمِعْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَبْلَ وَفَاتِهِ بِثَلَاثٍ يَقُولُ:
«لَا يَمُوتَنَّ أَحَدُكُمْ إِلَّا وَهُوَ يُحْسِنُ بِاللهِ الظَّنَّ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2877]
المزيــد ...

ከጃቢር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከመሞታቸው ሶስት ቀናት በፊት እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦
"አንዳችሁ በአላህ ላይ ያለውን እሳቤ ሳያሳምር እንዳይሞት።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2877]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሙስሊም በአላህ ላይ ያለውን እሳቤ አሳምሮ ካልሆነ በቀር እንዳይሞት አነሳሱ። ይህም ጣእረ ሞት ላይ የሆነ ጊዜ አላህ እንደሚያዝንለትና ይቅር እንደሚለው በማሰብ ተስፈኝነቱን በማመዘን ነው። በሸሪዓ አላህን መፍራት የተፈለገው ስራችንን እንድናሳምር ስለሚረዳን ነው። ይህ ያለበት ሁኔታ ደግሞ የስራ ሁኔታ አይደለምና በዚህ ሁኔታ ላይ የሚፈለገው ተስፈኝነትን ማመዘን ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية النيبالية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ኡመታቸውን በማቅናት (በማመላከት) ላይ ያላቸውን ጥረትና በሁሉም ሁኔታቸው ላይ ለኡመታቸው ያላቸውን ከፍተኛ እዝነት እንረዳለን። በሞቱበት በሽታ ላይ ሆነው እንኳ ኡመታቸውን ይመክራሉም የመዳን መንገድንም ይጠቁማሉ።
  2. ጢቢይ እንዲህ ብለዋል: "በምትሞቱ ወቅት በአላህ ላይ የሚኖራችሁ እሳቤ ያማረ እንዲሆን ዛሬ ላይ ስራችሁን አሳምሩ። ከመሞቱ በፊት ስራውን ያበላሸ ሰው በሚሞትበት ወቅትም እሳቤው ይበላሻልና።"
  3. ለአንድ ባሪያ የተሟላ የሚባለው ፍርሃቱና ተስፋው ተመጣጣኝ ሆነው ውዴታው ሲያመዝን ነው። ውዴታ መርከቧ ናት፤ ተስፋ ቀዛፊው ነው፣ ፍርሃት ሹፌሩ ነው። አላህ ደግሞ በችሮታውና በጸጋው አድራሹ ነው።
  4. ጣዕረ ሞት ላይ ወደሆነ ሰው የቀረበ ሰው ጣዕረ ሞት ላይ ላለው ሰው ተስፈኝነትንና በአላህ ያለውን እሳቤ ማሳመርን እንዲያመዝን ማድረግ ይገባዋል። እዚህ ሐዲሥ ውስጥም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህን የተናገሩት ከመሞታቸው ሶስት ቀን በፊት እንደሆነ ተዘግቧል።