1. ዋና ገጽ
  2. ምድቦች
  3. ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ሐዲሥ የመልካም ጓደኛና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌ እንደ ሽቶ ተሸካሚና እንደወናፍ ነፊ ነው።

عَنْ أَبِي مُوسَى رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّمَا مَثَلُ الْجَلِيسِ الصَّالِحِ وَالْجَلِيسِ السَّوْءِ كَحَامِلِ الْمِسْكِ وَنَافِخِ الْكِيرِ، فَحَامِلُ الْمِسْكِ: إِمَّا أَنْ يُحْذِيَكَ، وَإِمَّا أَنْ تَبْتَاعَ مِنْهُ، وَإِمَّا أَنْ تَجِدَ مِنْهُ رِيحًا طَيِّبَةً، وَنَافِخُ الْكِيرِ: إِمَّا أَنْ يُحْرِقَ ثِيَابَكَ، وَإِمَّا أَنْ تَجِدَ رِيحًا خَبِيثَةً».

ከአቡ ሙሳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ:
"የመልካም ጓደኛና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌ እንደ ሽቶ ተሸካሚና እንደወናፍ ነፊ ነው። ሽቶ ተሸካሚ ወይ ይሰጥሀል፣ ወይ ትገዛዋለህ፣ ወይ ከርሱ መልካም መአዛን ታገኛለህ። ወናፍ ነፊ ደግሞ ወይ ልብስህን ያቃጥላል ወይም ከርሱ መጥፎ ሽታን ታገኛለህ።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 2628

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለት አይነት ሰዎችን በምሳሌ ገለፁ።
የመጀመሪያው አይነት: ወደ አላህ የሚጠቁም፣ ወደ አላህ ውዴታ የሚመራና በአምልኮ ላይ የሚያግዝ መልካም ጓደኛ ነው። የርሱም ምሳሌ ሽቶ እንደሚሸጥ ሰው ምሳሌ ነው። ወይ ይሰጥሀል፣ ወይ ትገዛዋለህ፣ ወይም ከርሱ መልካም መአዛን ታሸታለህ።
ሁለተኛው አይነት ደግሞ ከአላህ መንገድ የሚያቅብ፣ ወንጀል በመፈፀም ላይ የሚያግዝ ፣ መጥፎ ተግባራትን የምታይበት መጥፎ ጓደኛ ነው። የሱን አይነት ሰው ወዳጅና ጓደኛ አድርገህ በመያዝህም የሚያስወቅስህ ነው። የርሱም ምሳሌ ወናፍ እንደሚያናፋ ብረት ቀጥቃጭ ነው። እርሱም ወይ በሚፈነጣጠረው እሳት ልብስህን ያቃጥላል ወይም ወደርሱ በመቅረብህ መጥፎ ሽታን ታገኛለህ።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. አዳማጩ ሀሳቡ እንዲገባው ምሳሌ ማድረግ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
  2. የመልካምና የበጎ ባለቤቶችን በመቀማመጥ ላይና የብክለትና የመጥፎ ስነ ምግባር ባለቤቶችን በመራቅ ላይ መነሳሳቱና መበረታታቱን እንረዳለን።

ትርጉሞችን አሳይ

56 ቋንቋ
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
YO Yorùbá اليوروبا
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
SO Soomaali الصومالية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
CS Čeština التشيكية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
AZ Azərbaycan الأذربيجانية
UZ O‘zbek الأوزبكية
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية
KMR Kurmancî الكرمنجية