عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللهُ عَنْهُمَا قَالَ:
كَانَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَليهِ وَسَلَّمَ لا يَعْرِفُ فَصْلَ السُّورةِ حَتَّى تَنْزِلَ عَليْهِ {بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ}.
[صحيح] - [رواه أبو داود] - [سنن أبي داود: 788]
المزيــد ...
ኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ ብሏል፦
" {ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒም} እስክትወርድ ድረስ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የምዕራፎችን መለያ አያውቁም ነበር።"
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 788]
የተከበረው ቁርኣን ምዕራፎች በነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ ሲወርዱ የሚጠናቀቁበትና ከሌላው ምእራፍ የሚለዩበትን መንገድ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አያውቁም ነበር። ይህ ግን {ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒም} እስክትወርድ ድረስ ነበር። እሷ ከወረደች በኋላ ያለፈው ምእራፍ እንደተጠናቀቀችና {ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒም} ለአዲስ ምዕራፍ መክፈቻ እንደሆነች አወቁ በማለት ኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ገለፁ።