عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بنِ مسعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ:
ذُكِرَ عِنْدَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ رَجُلٌ نَامَ لَيْلَهُ حَتَّى أَصْبَحَ، قَالَ: «ذَاكَ رَجُلٌ بَالَ الشَّيْطَانُ فِي أُذُنَيْهِ، أَوْ قَالَ: فِي أُذُنِهِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 3270]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ እስኪነጋ ድረስ ምሽቱን የተኛ ሰውዬ ተወሳ። እርሳቸውም "ይህ ሸይጧን ጆሮዎቹ ውስጥ ወይም ጆሮው ውስጥ የሸናበት ሰው ነው።" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3270]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ እስኪነጋና ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ የተኛ፤ ግዴታ ሶላትን ለመስገድም ስላልተነሳ ሰውዬ ተወሳ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህ ሸይጧን ጆሮው ውስጥ የሸናበት ሰው ነው አሉ።