عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بِن مَسْعُودٍ رضي الله عنه قَالَ:
سَأَلْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: أَيُّ العَمَلِ أَحَبُّ إِلَى اللَّهِ؟ قَالَ: «الصَّلاَةُ عَلَى وَقْتِهَا»، قَالَ: ثُمَّ أَيٌّ؟ قَالَ: «ثُمَّ بِرُّ الوَالِدَيْنِ» قَالَ: ثُمَّ أَيٌّ؟ قَالَ: «الجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ» قَالَ: حَدَّثَنِي بِهِنَّ، وَلَوِ اسْتَزَدْتُهُ لَزَادَنِي.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 527]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦
"ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስራ ምን እንደሆነ ጠየቅኳቸው። እሳቸውም 'ሶላትን በወቅቱ መስገድ።' አሉ። 'ከዚያስ ቀጥሎ' አልኳቸው። እርሳቸውም 'ቀጥሎ ለወላጆች መልካም መዋል ነው።' አሉኝ። 'ከዚያስ ቀጥሎ' አልኳቸው። እርሳቸውም 'በአላህ መንገድ መታገል ነው።' አሉ። እነዚህን ነገሩኝ። ጥያቄዬን ብጨምር እርሳቸውም ይጨምሩልኝ ነበር።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 527]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስራ ምን እንደሆነ ተጠየቁ። እርሳቸውም "ግዴታ ሶላቶችን አላህ በገደበው ወቅት መስገድ ነው።" ብለው መለሱ። ቀጥሎም በጎ በማድረግ፣ ሐቃቸውን በመጠበቅ፣ ሐቃቸውን ከመጨፍለቅ በመቆጠብ ለወላጆች መልካም መዋል ነው። ቀጥሎም የአላህን ንግግር የበላይ ለማድረግ፣ ከኢስላምና ከተከታዮቹ ጠላቶችን ለመመከትና የኢስላምን ምልክቶች ይፋ ለማድረግ በአላህ መንገድ መታገል ነው። ይህም በነፍስና በገንዘብ ነው።
ኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እነዚህን ስራዎች ነገሩኝ። ለርሳቸው 'ከዚያስ ቀጥሎ' ብላቸው ኖሮ ግን ይጨምሩልኝ ነበር።" አሉ።