1. ዋና ገጽ
  2. ምድቦች
  3. ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ሐዲሥ ከስለት ከለከሉ። እንዲህም አሉ "እርሱ መልካምን ይዞ አይመጣም። በስለት የሚገኘው ትርፍ ስስታም ተገዶ ማውጣቱ ብቻ ነው።

عَنِ ابْنِ عُمَرَ رضي الله عنهما:
عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنَّهُ نَهَى عَنِ النَّذْرِ، وَقَالَ: «إِنَّهُ لَا يَأْتِي بِخَيْرٍ، وَإِنَّمَا يُسْتَخْرَجُ بِهِ مِنَ الْبَخِيلِ».

ኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዳስተላለፉት:
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ‐ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ‐ ከስለት ከለከሉ። እንዲህም አሉ "እርሱ መልካምን ይዞ አይመጣም። በስለት የሚገኘው ትርፍ ስስታም ተገዶ ማውጣቱ ብቻ ነው።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 1639

ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከስለት ከለከሉ። ይህም አንድ ሰው አላህ ግዴታ ያላደረገበትን ነገር በራሱ ላይ ግዴታ ማድረጉ ማለት ነው። እንዲህም አሉ: ስለት አንድን ነገር አያመጣምም አያዘገይምም። ከስለት የሚገኘው ግዴታ የሆነበትን ነገር ካልሆነ በቀር የማይፈፅምን የሆነ ስስታም ሰው ተገዶ እንዲያወጣ ማስድረጉ ነው። ስለት ያልተወሰነልህን ነገር አያመጣም።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. ስለት መሳል አልተደነገገም፤ ነገር ግን ከወንጀል ውጪ ከተሳለ ስለቱን መሙላት ግዴታው ነው።
  2. የክልከላው ምክንያት (ስለት መልካምን ይዞ አይመጣም) ማለትም ከአላህ ውሳኔ አንዳችንም አይመልስምና፤ የተሳለው ሰውም ፍላጎቱ የተሟላው በስለቱ ምክንያት መሆኑን እንዳያስብ ነው። አላህ ከዚህ የተብቃቃ ነውና።
  3. ቁርጡቢ እንዲህ ብለዋል: «ይህ ክልከላ ለምሳሌ እንዲህ ማለቱን ነው: "አላህ የታመመብኝን ከፈወሰልኝ እኔ ላይ እንዲህ ያህል ምፅዋት አለብኝ።" ይህ የተጠላበትም ምክንያት የተጠቀሰውን አምልኮ መፈፀም ከተጠቀሰው አላማ መሳካት ጋር ያቆራኘ በመሆኑ ከርሱ የሚመነጨው ተግባር ወደ አላህ በመቃረብ ኒያ ሳይሆን ይልቁኑም የሄደበት መንገድ የመለዋወጥ ስልት መሆኑ ግልፅ ነው። ይህንንም የበለጠ ግልፅ የሚያደርግልን ታማሚው ባይፈወስለት ኖሮ በመፈወሱ ምክንያት ያወጣው የነበረውን ምፅዋት አለማውጣቱ ነው። ይህ ደግሞ የስስታሞች መገለጫ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ስስታም ሰው ከሚያወጣው ወጪ በላይ ተለዋጭ ጥቅም በወቅቱ እስካላስገኘለት ድረስ ከገንዘቡ አንዳችንም አያወጣምና።

ትርጉሞችን አሳይ

55 ቋንቋ
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
YO Yorùbá اليوروبا
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
SO Soomaali الصومالية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
CS Čeština التشيكية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
AZ Azərbaycan الأذربيجانية
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية