+ -

عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بنِ عُمَرَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُما:
أَنَّ امْرَأَةً وُجِدَتْ فِي بَعْضِ مَغَازِي النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ مَقْتُولَةً، فَأَنْكَرَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَتْلَ النِّسَاءِ وَالصِّبْيَانِ.

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 3014]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
አንዲት ሴት ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በተሳተፉበት አንድ ጦርነት ላይ ተገድላ ተገኘች። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሴትና ህፃናትን መግደልን አወገዙ።

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3014]

ትንታኔ

በአንድ ጦርነት ወቅት ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንዲት ሴት መገደሏን ተመለከቱ። እርሳቸውም የሴትንና ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ህፃናት መገደልን አወገዙ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الرومانية Malagasisht Oromisht Kannadisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከሴትና ከህፃናት ሆነው እንዲሁም እንደነሱ ደካሞች የሆኑ የጃጁ ሽማግሌዎችና ባህታዊዎች በስትራቴጂ እውቀታቸው ሙስሊሞችን በመዋጋት ላይ የሚያግዙ ካልሆኑ በቀር አይገደሉም። እንደዚህ ሆነው ከተገኙ ግን ይገደላሉ።
  2. ሴቶችና ህፃናትን መግደል መከልከሉን እንረዳለን። ይህም እነዚህ አካላት ሙስሊሞችን ስለማይዋጉ ነው። በአላህ መንገድ የመታገል ዋነኛ አላማው የእውነት ጥሪ ወደ ሰዎች ባጠቃላይ እስኪደርስ ድረስ የሚያቅቡ አካላትን ሀይል መስበር ብቻ ነውና።
  3. በዘመቻዎችና ጦርነቶች ሳይቀር የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እዝነት ምን ያህል እንደነበር እንረዳለን።