+ -

عَنْ جَابِرٍ رضي الله عنه قَالَ:
أَتَى النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ رَجُلٌ فَقَالَ: يَا رَسُولَ اللهِ، مَا الْمُوجِبَتَانِ؟ فَقَالَ: «مَنْ مَاتَ لَا يُشْرِكُ بِاللهِ شَيْئًا دَخَلَ الْجَنَّةَ، وَمَنْ مَاتَ يُشْرِكُ بِاللهِ شَيْئًا دَخَلَ النَّارَ»

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 93]
المزيــد ...

ጃቢር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦
ወደ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ዘንድ አንድ ሰውዬ በመምጣት እንዲህ አለ፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሁለቱ (ጀነትና እሳትን) የሚያስወስኑ ነገሮች ምንድናቸው?" እሳቸውም "በአላህ ላይ አንዳችንም ሳያጋራ የሞተ ሰው ጀነት ገባ፤ በአላህ ላይ አንዳችን እያጋራ የሞተ ሰው እሳት ገባ።" አሉ።

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 93]

ትንታኔ

አንድ ሰውዬ ነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ጀነት መግባትን ስለሚያስወስን እና እሳት መግባትን ስለሚያወስን ሁለት ነገሮች ጠቃቸው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን፦ ጀነትን የሚያስወስነው ነገር ሰውዬው አላህን በብቸኝነት እያመለከ በሱ አንዳችንም ሳያጋራ መሞቱ ነው ብለው መለሱለት። እሳትን የሚያስወስነው ነገር ደግሞ ሰውዬው ለአላህ በተመላኪነቱ ወይም በጌትነቱ ወይም በስሞቹና ባህሪያቶቹ መሳይ እና አቻ በማድረግ በአላህ ላይ አንዳችን ነገር እያጋራ መሞቱ ነው ብለው መለሱለት።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የተውሒድ ትሩፋት መገለፁ። እሱም አማኝ ሆኖ በአላህ ላይ አንዳችንም ሳያጋራ የሞተ ሰው ጀነት የሚገባ መሆኑን።
  2. የሺርክ አደገኝነትም መገለፁ። እሱም፥ በአላህ ላይ አንዳችን እያጋራ የሞተ ሰው እሳት የሚገባ መሆኑን።
  3. ከተውሒድ ሰዎች መካከል፥ ወንጀል የሰሩ በአላህ ፍላጎት እና ውሳኔ ስር መሆናቸው፤ በመሆኑም ከፈለገ እንደሚቀጣቸው ከፈለገም የሚምራቸው እንድሆነ እና ከዚያም መመለሻቸው ወደ ጀነት መሆኑን።
ተጨማሪ