عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رضي الله عنهما عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَنْ عَادَ مَرِيضًا، لَمْ يَحْضُرْ أَجَلُهُ فَقَالَ عِنْدَهُ سَبْعَ مِرَارٍ: أَسْأَلُ اللَّهَ الْعَظِيمَ رَبَّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ أَنْ يَشْفِيَكَ، إِلَّا عَافَاهُ اللَّهُ مِنْ ذَلِكَ الْمَرَضِ».
[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي وأحمد] - [سنن أبي داود: 3106]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዐባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ሞቱ ያልቀረበን በሽተኛ የጠየቀና እርሱ ዘንድ ሰባት ጊዜ "አስአሉሏሀል ዐዚም ረበል ዐርሺል ዐዚም አንየሽፊከ" ካለ አላህ ከዛ ካመመው በሽታ ያድነዋል።" ትርጉሙም "ታላቁ አላህን የታላቁን ዐርሽ ጌታ እንዲፈውስህ እጠይቃለሁ።" ማለት ነው።
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 3106]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንድም ሙስሊም የሞቱ ወቅት ያልቀረበበትን ሙስሊም በሽተኛ ሲጎበኝ: (ታላቁን አላህ እጠይቀዋለሁ።) በዛቱ፣ በባህሪያቱና በድርጊቶቹ (የታላቁን ዐርሽ ጌታ እንዲፈውስህ) እያለ ሰባት ጊዜ ዱዓ ካደረገለት አላህ ከዛ በሽታ ይፈውሰዋል በማለት ተናገሩ።