1. ዋና ገጽ
  2. ምድቦች
  3. ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ሐዲሥ ረመዳን የገባ ጊዜ የጀነት በሮች ይከፈታሉ፤ የእሳት በሮችም ይዘጋሉ፤ ሰይጣኖችም ይጠፈነጋሉ።

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللهُ عَنْهُ أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، قَالَ:
«إِذَا جَاءَ رَمَضَانُ فُتِّحَتْ أَبْوَابُ الْجَنَّةِ، وَغُلِّقَتْ أَبْوَابُ النَّارِ، وَصُفِّدَتِ الشَّيَاطِينُ».

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦
"ረመዳን የገባ ጊዜ የጀነት በሮች ይከፈታሉ፤ የእሳት በሮችም ይዘጋሉ፤ ሰይጣኖችም ይጠፈነጋሉ።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 1079

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የረመዷን ወር የገባ ጊዜ ሶስት ነገሮች እንደሚከሰቱ ተናገሩ:- አንደኛ: የጀነት በሮች ይከፈታሉ። ከጀነት በሮችም አንድም በር አይዘጋም። ሁለተኛ: የእሳት በሮች ይዘጋሉ። አንድም የእሳት በር አይከፈትም። ሶስተኛ: ሰይጣኖችና አመፀኛ ጋኔኖች በሰንሰለት ይጠፈነጋሉ። ከረመዷን ውጪ ይደርሱበት ወደነበረው አይደርሱም። ይህ ሁሉ ለዚህ ወር ልቅና፣ ከሶላት፣ ከሶደቃ፣ ከዚክር፣ ቁርአን ከመቅራትና ከዛም ውጪ ያሉ አምልኮዎች በማብዛት ላይና ከወንጀሎችና ከሀጢአቶች በመራቅ ላይ ሰሪዎችን ለማነሳሳት ነው።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. የረመዷን ወር ደረጃን እንረዳለን
  2. ይህ የተከበረ ወር የአምልኮና የመልካም ተግባር ወቅት ከመሆኑ አኳያ ይህ ሐዲሥ ለጾመኞች ብስራት ነው።
  3. ረመዷን ውስጥ ሸይጣኖች መጠፍነጋቸው የትኛውም ለአቅመ አዳም የደረሰ ሰው ወንጀል ለመስራት ምክንያት እንደሌለው ለመጠቆም ነው። "ሸይጣኖች ወደ አንተ እንዳይቀርቡ ስለተጠበቅክ አምልኮ ለመተውህና ወንጀልን ለመስራትህ እነርሱን ምክንያት እንዳታደርግ።" የተባለ ነው የሚመስለው።
  4. ቁርጡቢይ እንዲህ ብለዋል: «"በረመዳን ውስጥ ብዙ ክፋትና ወንጀሎች ሲከሰት እንዴት እናያለን? ሸይጣኖች ቢታሰሩ ኖሮ ይህ አይከሰትም ነበር።" ቢባል። መልሱ: ክፋቶችና ወንጀሎች የሚያንሱት መስፈርቶቹን የጠበቀና ስነስርዓቱን ያሟላን ጾም ከጾሙ ሰዎች ላይ ነው። ወይም የሚታሰሩት በአንዳንድ ዘገባዎች ቀደም ተብሎ እንደተጠቀሰው ሁሉም ሳይሆኑ አመፀኛ የሆኑት የተወሰኑ ሸይጣኖች ብቻ ናቸው። ወይም በሐዲሡ የተፈለገው ክፋቶች እንደሚያንሱ መጥቀስ ነው። ይህም ደግሞ በገሃድ የሚታይ ነገር ነው። ከሌላ ጊዜ በተለየ ወንጀሎች በረመዷን መከሰታቸው እጅግ የመነመነ ነውና። በተጨማሪም ሁሉም ሸይጣኖች በመታሰራቸው ክፋትና ወንጀል አይከሰትም የሚለውን አያሲዝም። ወንጀል ለመስራት እንደ ቆሸሸች ነፍስ፣ መጥፎ ልምዶችና የሰው ሸይጣኖችን የመሰሉ ከጂን ሸይጣን ውጪ ያሉ ሌሎች ምክንያቶችም ስላሉ።

ትርጉሞችን አሳይ

43 ቋንቋ
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية