1. ዋና ገጽ
  2. ምድቦች
  3. ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ሐዲሥ በአላህ መንገድ ላይ አንድ ቀን የጾመ ሰው አላህ ፊቱን ከእሳት ሰባ ዓመታት ያርቀዋል።

عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ رَضِيَ اللهُ عَنْهُ قَالَ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«مَنْ صَامَ يَوْمًا فِي سَبِيلِ اللهِ بَاعَدَ اللهُ وَجْهَهُ عَنِ النَّارِ سَبْعِينَ خَرِيفًا».

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ:
"በአላህ መንገድ ላይ አንድ ቀን የጾመ ሰው አላህ ፊቱን ከእሳት ሰባ ዓመታት ያርቀዋል።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 1153

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንድ ቀን በጂሃድ ላይ እያለ የጾመ ሰው፤ ‐ በጂሃድም ሆነ ከዛ ውጪ እያለ የአላህን ምንዳና አጅር ፈልጎ ለአላህ አጥርቶ የፆመ ማለት ነውም ተብሏል። ‐ አላህ በችሮታው በርሱና በእሳት መካከል ሰባ ዓመታትን ያራርቃል ብለው ገለፁ።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: «በአላህ መንገድ ላይ ሆኖ መጾም የሚያስገኘው ትሩፋት የሚተረጎመው በመጾሙ የማይጎዳ ለሆነ፤ በመጾሙ የሌሎችን ሐቆች የማያስመልጥ ለሆነ፤ የመዋጋቱና ሌሎች የጦርነት ግዳጆቹ ላይ የማያጓድል ለሆነ ሰው ነው።»
  2. ሱና ጾም በመጾም ላይ መነሳሳቱንና መበረታታቱን እንረዳለን።
  3. ሥራን ለአላህ ማጥራትና በርሱ የአላህን ውዴታ መፈለግ ግዴታ ነው። ለይዩልኝ፣ ለይስሙልኝና ለሌሎች አላማ ብሎ መጾም የለበትም።
  4. ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: «ሐዲሡ ውስጥ (በአላህ መንገድ) የሚለው ኒያን ማስተካከል ብቻ (ለአላህ ብሎ) በማለትም ሊተረጎም ይችላል፤ ዘመቻ ላይ ሆኖ የጾመ በማለት ሊተረጎምም ይችላል። ወደ አዕምሮ ፈጥኖ የሚገባው ሀሳብ ግን ሁለተኛው ትርጉም ነው።»
  5. ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: ሐዲሡ ውስጥ (ሰባ መኸር) የሚለው ንግግር: መኸር ከዓመቱ ወቅቶች ውስጥ የሚታወቅ ጊዜ ያለው ወቅት ነው። ሐዲሡ ውስጥ የተፈለገው ግን ዓመትን ለመግለፅ ነው። ሌሎችን የዓመቱ ክፍለጊዜያት (በጋ፣ክረምት፣ በልግን) ትተው መኸርን ለይተው የጠቀሱት መኸር ዘር የሚቀጠፍበት ምርጡ ክፍለጊዜ ስለሆነ ነው።

ትርጉሞችን አሳይ

47 ቋንቋ
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
NE नेपाली النيبالية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية