+ -

عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المؤْمِنينَ رَضِيَ اللهُ عَنْهَا:
كَانَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَجْتَهِدُ فِي الْعَشْرِ الْأَوَاخِرِ مَا لَا يَجْتَهِدُ فِي غَيْرِهِ.

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1175]
المزيــد ...

የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው፦
"የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሌላ ጊዜያት ለአምልኮ ከሚጥሩት የተለየ በመጨረሻዎቹ አስሩ የረመዷን ቀናት ይጥሩ ነበር።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1175]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የመጨረሻዎቹ አስሩ የረመዷን ቀናት የመጡ ጊዜ በአምልኮና ትርፍ ስራዎች ላይ ጥረት ያደርጉ ነበር። በሌላ ወቅት ይጥሩ ከነበሩት የበለጠ በመልካም ስራ አይነቶች፣ በአምልኮና፣ በበጎ አድራጎት ዘርፎች አበዝተው ይጥሩ ነበር። ይህም እንዚህ ሌሊቶች ያላቸው ደረጃ የላቀና ከፍያለ ስለሆነ እንዲሁም ለይለተል ቀደርንም ለመፈለግ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية النيبالية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በረመዷን ወር ባጠቃላይ በተለይ የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ላይ መልካም ስራዎችንና የተለያዩ አምልኮዎችን በማብዛት መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. የመጨረሻዎቹ አስር የረመዷን ቀናት ከሀያ አንደኛው ምሽት ጀምሮ እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ ይሄዳል።
  3. የላቁ ወቅቶችን በአምልኮ ማሳለፍ እንደሚወደድ እንረዳለን።