عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللهُ عَنْهُمَا:
أَنَّ نَاسًا مِنْ أَهْلِ الشِّرْكِ، كَانُوا قَدْ قَتَلُوا وَأَكْثَرُوا، وَزَنَوْا وَأَكْثَرُوا، فَأَتَوْا مُحَمَّدًا صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَقَالُوا: إِنَّ الَّذِي تَقُولُ وَتَدْعُو إِلَيْهِ لَحَسَنٌ، لَوْ تُخْبِرُنَا أَنَّ لِمَا عَمِلْنَا كَفَّارَةً، فَنَزَلَ {وَالَّذِينَ لا يَدْعُونَ مَعَ اللهِ إِلَهًا آخَرَ وَلا يَقْتُلُونَ النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللهُ إِلا بِالْحَقِّ وَلا يَزْنُونَ}[الفرقان: 68]، وَنَزَلَت: {قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَى أَنْفُسِهِمْ لا تَقْنَطُوا مِنْ رَحْمَةِ اللهِ} [الزمر: 53].
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 4810]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል:
"ከዚህ በፊት አብዝተው ነፍስ የሚገድሉ፣ አብዝተው ዝሙት የሚሰሩ የነበሩ የሺርክ ባለቤት የሆኑ ሰዎች ሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዘንድ በመምጣት እንዲህ አሉ ' የምትናገረውና የምትጣራበት ጉዳይ መልካም ነው። ለሰራነው ፀያፍ ተግባር ማስማሪያ እንዳለው እንደው ብትነግረን?' {እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይግገዙት፤ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ህግ የማይገድሉት፤ የማያመነዝሩትም ናቸው።} [ፉርቃን:68] የሚለውና {በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ።»} [አዝዙመር: 53] የሚለው አንቀፅ ወረደች።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 4810]
ከሙሽሪኮች የሆኑ ሰዎች ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መጡ። አብዝተው የገደሉና የዘሞቱ ነበሩ። ለነቢዩ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: የምትጣራው ኢስላምና አስተምህሮቶቹ መልካም ጉዳይ ነው። ነገር ግን የወደቅንበት ሺርክና ከባድ ወንጀል ለርሱ ማስማሪያ አለውን?
ወንጀላቸው ከመብዛቱና ከመተለቁ ጋርም አላህ ከሰዎቹ ተውበታቸውን እንደተቀበለ የሚጠቁሙ ሁለት አንቀፆች ወረዱ። ይህ ባልነበር ኖሮ በክህደታቸውና ጥመታቸው ላይ ይቀጥሉ ነበር። ወደዚህ ሃይማኖትም አይገቡም ነበር።