عَنْ عَبْدِ اللهِ بنِ عُمَر رضي الله عنهما قال: قال رسولُ الله صلى الله عليه وسلم:
«بُنِيَ الْإِسْلَامُ عَلَى خَمْسٍ: شَهَادَةِ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُهُ وَرَسُولُهُ، وَإِقَامِ الصَّلَاةِ، وَإِيتَاءِ الزَّكَاةِ، وَحَجِّ الْبَيْتِ، وَصَوْمِ رَمَضَانَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 16]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
«እስልምና በአምስት መሰረቶች ተገነባ እነርሱም: 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወአንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛ ናቸው።) ብሎ መመስከር፣ ሶላትን ማቋቋም፣ ዘካ መስጠት፣ በተከበረው የአሏህ ቤት ሐጅ ማድረግ እና የረመዷንን ወር መፆም ናቸው።'»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 16]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ኢስላምን አምስት አስተማማኝ ምሶሶዎች እንደተሸከሙት ቤት አድርገው መሰሉት። የተቀሩትን የኢስላም ጉዳዮች ደግሞ ቤቱን እንደሚያሟሉ ነገሮች ናቸው። ከእነዚህ ማእዘናት የመጀመሪያው: ሁለቱ የምስክርነት ቃላት ናቸው። እነርሱም: ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን መመስከር ነው። እነዚህ ሁለቱ የምስክርነት ቃላት እንደ አንድ ማእዘን ናቸው። አንዱ ከሌላኛው ተለይቶ የሚታይ አይደለምና። የአላህን ብቸኛ መሆንና ከርሱ ውጪ ያለውን ትቶ በብቸኝነት ለአምልኮ የተገባው እርሱ ብቻ መሆኑን በማመን፣ የሚያስፈርዱትን በመተግበር፣ በሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መልዕክተኝነታቸውን በማመንና እርሳቸውን በመከተል አንድ ባሪያ እነዚህን ሁለት የምስክርነት ቃላት ይናገራል። ሁለተኛው ማእዘን: በቀንና በምሽት የሚሰገዱ የሆኑት የፈጅር፣ የዙህር፣ የዐስር፣ የመጝሪብ እና የዒሻእ ሶላቶችን መስፈርቶቹን፣ ማእዘናቶቹንና ግዴታዎቹን ጠብቆ ማቋቋም ነው። ሶስተኛው ማእዘን: ግዴታ የሆነውን ዘካ ማውጣት ነው። ይህም ገንዘቡ በሸሪዓ የተወሰነውን ያህል መጠን የደረሰ ባለገንዘብ በሙሉ፤ ለሚገባው አካል ሊሰጥ ግዴታ የተደረገበት ገንዘባዊ አምልኮ ነው። አራተኛው ማእዘን: ሐጅ ነው። እርሱም: አምልኳዊ በሆነ መልኩ የሐጅ ተግባራትን ለመፈፀም መካን ማሰብ ነው። አምስተኛው ማእዘን: ረመዷንን መፆም ነው። እርሱም: አላህን በማምለክ ኒያ ጎህ ከወጣችበት ሰአት ጀምሮ ፀሀይ እስከምትጠልቅ ድረስ ከመብላት፣ ከመጠጣትና ሌሎችም ፆምን ከሚያስፈጥሩ ነገሮች መቆጠብ ማለት ነው።