عَنْ أَبِي الدَّرْدَاءِ رضي الله عنه: سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«إِنَّ اللَّعَّانِينَ لَا يَكُونُونَ شُهَدَاءَ وَلَا شُفَعَاءَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2598]
المزيــد ...
ከአቡ ደርዳእ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:
"ተራጋሚዎች የትንሳኤ ቀን መስካሪዎችም ሆነ አማላጅ አይሆኑም።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2598]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላግባብ እርግማን የሚያበዛ ሰው ለሁለት ቅጣቶች እንደሚዳረግ ተናገሩ: የመጀመሪያው: የትንሳኤ ቀን መልክተኞች ለህዝቦቻቸው ተልእኳቸውን እንዳደረሱ ከሚመሰክሩ ምስክሮች አይሆኑም፤ አመፀኛ ስለሆነም በዱንያም ምስክርነቱ ተቀባይነት አይኖረውም፤ ሰማዕትነትንም እርሱም በአላህ መንገድ መገደል ስለሆነ አይገጠምም። ሁለተኛው: አማኞች የትንሳኤ ቀን እሳት መግባት ግድ የሆነባቸውን ወንድሞቻቸውን በሚያማልዱበት ጊዜ እነርሱ ግን አያማልዱም።