+ -

عَن ابنِ عباسٍ رضي الله عنهما أنَّ رسولَ اللهِ صلي الله عليه وسلم قال:
«لَو يُعطَى النّاسُ بدَعواهُم لادَّعَى رِجالٌ أموالَ قَومٍ ودِماءَهُم، ولَكِنَّ البَيِّنَةَ على المُدَّعِى، واليَمينَ على مَن أنكَرَ».

[صحيح] - [رواه البيهقي] - [السنن الكبرى للبيهقي: 21243]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ሰዎች በመክሰሳቸው ብቻ ቢሰጣቸው ኖሮ ሰዎች የሌሎችን ገንዘብና ደም (ለመውሰድ) ይከሱ ነበር። ነገር ግን ማስረጃ በከሳሽ ላይ፣ መሀላ ደግሞ ባወገዘ ሰው ላይ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ተደረገ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [Al-Bayhaqi] - [السنن الكبرى للبيهقي - 21243]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሰዎች ያለማስረጃና ያለ ጠቋሚ ማስረጃ በመክሰሳቸው ብቻ ቢሰጣቸው ኖሮ ሰዎች የሌሎችን ገንዘብና ደም ለመውሰድ ይከሱ እንደነበር፤ ነገር ግን ከሳሽ ለፈለገው ጉዳይ ማስረጃ የማስቀደም ግዴታ እንዳለበት ማስረጃ ከሌለው ደግሞ ክሱ ወደ ተከሳሽ ይቀርብና ክሱን ካወገዘው በመማል ራሱን ከጥፋተኝነት እንደሚያነፃ ገለፁ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية النيبالية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ኢብኑ ደቂቅ አልዒዲ እንዲህ ብለዋል: «ይህ ሐዲሥ ከህግጋቶች መሰረት መካከል አንዱ መሰረትና በንትርክና መካሰስ ወቅት የምንጠቀመው ትልቅ ምንጭ (መመለሻ) ነው።»
  2. ሸሪዓ የሰዎችን ገንዘብና ደም ከመጫወቻነት ለመጠበቅ የመጣ እንደሆነ እንረዳለን።
  3. ዳኛ በእውቀቱ አይፈርድም። ይልቁንም ፍርድ የሚመለሰው ወደ ማስረጃ ነው።
  4. ማንኛውንም ሙግት የሞገተና ሙግቱ ከማስረጃ የፀዳ ከሆነ ተመላሽ ነው። ይህም በመብቶችም፣ በግብይይትም ይሁን በኢማንና እውቀት ዙሪያም የሚሰራ መርህ ነው።
ተጨማሪ