1. ዋና ገጽ
  2. ምድቦች
  3. ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ሐዲሥ ለይለቱል ቀድርን በረመዷን የመጨረሻ አስር ቀናቶች በጎደሎ ቁጥሮቹ ውስጥ ፈልጓት።

عَنْ عَائِشَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«تَحَرَّوْا لَيْلَةَ القَدْرِ فِي الوِتْرِ مِنَ العَشْرِ الأَوَاخِرِ مِنْ رَمَضَانَ».

ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ለይለቱል ቀድርን በረመዷን የመጨረሻ አስር ቀናቶች በጎደሎ ቁጥሮቹ ውስጥ ፈልጓት።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2017

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለይለቱል ቀድርን ለመፈለግ መልካም ስራዎችን በማብዛት መታገል እንደሚገባ አነሳሱ። ለይለቱል ቀድርም በሁሉም ዓመት ከረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት በጎዶሎው ምሽቶች መሆኗ ተስፋ ይደረጋል። እነርሱም: ሀያ አንደኛ፣ ሀያ ሶስተኛ፣ ሀያ አምስተኛ፣ ሀያ ሰባተኛና ሀያ ዘጠነኛ ሌሊቶች ናቸው።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. የለይለቱል ቀድርን ትሩፋትና እርሷን በመፈለግ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. ከአላህ ጥበብና እዝነት መካከል ሰዎች እርሷን ፍለጋ በአምልኮ ሲታገሉ ምንዳቸው እንዲጨምር ይህቺን ሌሊት መደበቁ ነው።
  3. ለይለቱል ቀድር በረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ ነው። በጎዶሎዎቹ ቀናት መሆኑም ይበልጥ ተስፋ ይደረጋል።
  4. ለይለቱል ቀድር ማለት ከረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ሌሊቶች መካከል አንዷ ናት። እርሷም አላህ ዐዘ ወጀል በነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ላይ ቁርአን ያወረደበት ሌሊት ናት። ይህችንም ሌሊት በበረከትና በደረጃዋ ታላቅነት ከአንድ ሺህ ወር የተሻለች አድርጓታል። ስለዚህም በዚህች ሌሊት መልካም ስራ መስራት ታላቅ ስፍራ ያለው ነው።
  5. (ለይለቱል ቀድር) ተብላ የተጠራቸው ወይ ልቅና ከሚለው ቃል ተወስዶ ነው። (እከሌ ቀድሩ ታላቅ ነው።) ማለትም ልቅናው ከፍ ያለ ነው ማለት ነው። ልክ እንደዚሁ ቀድሯ ትልቅ የሆነችው ሌሊት ሲባል "ቀድር" የሚለው ቃል ሌሊት ለሚለው ቃል ገላጭ ይሆናል። ማለትም የላቀችዋ (የተከበረችዋ) ሌሊት ማለት ነው። ማለትም ደረጃዋ፣ ልቅናዋና ስፍራዋ የላቀ ማለት ነው። {እኛ (ቁርአንን) በተባረከው ምሽት አወረድነው።} [አድዱኻን:3] ወይም ደሞ (ተቅዲር) መወሰኛ ከሚለው ቃል ነው የተወሰደችው ቢባልም ያስኬዳል። ማለትም በዚህች ምሽት ውስጥ በአመት ውስጥ የሚከሰተው ነገር ይወሰናል። {በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል።} [አድዱኻን:4]

ትርጉሞችን አሳይ

46 ቋንቋ
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
NE नेपाली النيبالية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية