1. ዋና ገጽ
  2. ምድቦች
  3. ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ሐዲሥ ውልደት ክልክል የሚያደርገውን ጥቢ ክልክል ታደርጋለች።

عَنْ عَائِشَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«الرَّضَاعَةُ تُحَرِّمُ مَا تُحَرِّمُ الوِلَادَةُ».

ከዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"ውልደት ክልክል የሚያደርገውን ጥቢ ክልክል ታደርጋለች።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። الأربعون النووية - 44

ማብራሪያ

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ውልደት እንደ ኻል (በእናት በኩል ያለ አጎት) ወይም ዐም (በአባት በኩል ያለ አጎት) ወይም ወንድም ወዘተ ክልክል እንደሚያደርገው ሁሉ ጥቢም የሚከለክል መሆኑን ገለፁ። ውልደት ሐላል የሚያደርገውን ህግጋትንም ጥቢም ሐላል ያደርገዋል።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. ይህ ሐዲሥ በጥቢ ህግ ዙሪያ መርህ የሆነ ሐዲሥ ነው።
  2. ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: (ውልደት ክልክል የሚያደርገውን ጥቢም ክልክል ታደርጋለች።) ማለታቸው ውልደት ፍቁድ የሚያደርገውን ነገር ጥቢም ፍቁድ ያደርገዋል ማለት ነው። ይህም በዑለማዎች ሁሉ ስምምነት መሰረት ጋብቻና ከጋብቻ ጋር የተያያዙ ክልከላዎችን የተመለከተ ነው። ክልከላው የሚመለከተውም በጠባው ልጅና በአጥቢዋ ልጆች መካከል ነው። እርስ በርስ መተያየት፣ ለብቻ ገለል ብለው መቀመጥና መገለጥ ከመፈቀዱ አንፃር እንደቅርብ ዘመድ ደረጃ ነው የሚተያዩት። ነገርግን የመወራረስ፣ ለአጥቢዋ ወጪ መቻል፣ አጥቢዋ ባሪያ ብትሆን ነፃ ማውጣት፣ የመግደል ጉማ ክፍያ መጋራት፣ ቂሳስን ውድቅ ማድረግና ሌሎች የተቀሩት የወላድ እናትነት ህግጋት ግን ጥቢን ተከትለው አይመጡም።
  3. በጥቢ ክልክል የመደረጉ ብይን እስከሞት የዘወተረ ክልከላን ነው የሚያፀናው።
  4. በሌሎች ሐዲሦች እንደተረጋገጠው በጥቢ ክልክል መደረጉ የሚረጋገጠው በታወቁ አምስት መጥባቶች ነው። እንዲሁም የጠባው በመጀመሪያ ሁለት አመቶች ውስጥ መሆን አለበት።
  5. በዘር ምክንያት ከነርሱ ጋር መጋባት ክልክል የሆኑ አካላት: እናቶች ‐ እዚህ ውስጥም በእናትም ይሁን በአባት በኩል ያሉ አያቶች ከፍ ቢሉ እንኳ ይካተታሉ‐ ፣ ልጆች ‐ የልጅ ልጆችም ወደታች ቢወርዱ እንኳ ይካተታሉ ‐ ፣ እህቶች ‐ በአባት በእናት የሚገናኙም ይሁኑ ወይም በአንዳቸው በኩል የሚገናኙ ቢሆኑም ተመሳሳይ ነው ‐ ፣ የአባት እህት (አክስት) ‐ እዚህ ውስጥም ከአባት ጋር በአባት በእናት የሚገናኙ እህቶቹም ይሁን በአንዱ በኩል የሚገናኙ እህቶቹ ቢሆኑም ሁሉም የአባት እህቶች ይካተታሉ። ልክ እንደዚሁ የአያቶች እህቶችም ይካተታሉ ‐ ፣ የእናት እህት ‐ ከእናት ጋር በአባትና በእናት የሚገናኙ እህቶቿም ይሁን በአንዱ በኩል የሚገናኙ እህቶቿ ቢሆኑም ሁሉም የእናት እህቶች ይካተታሉ። ልክ እንደዚሁ የሴት አያቶች እህቶችም የአባት እናትም ይሁኑ የእናት እናት ይካተታሉ ‐ ፣ የወንድም ሴት ልጆች፣ የእህት ሴት ልጆች ‐ እዚህ ውስጥም የእህትና የወንድም የልጅ ልጆችም ይካተታሉ‐።
  6. በዘር ምክንያት ከነርሱ ጋር መጋባት ክልክል የሆኑ ሴቶች በጥቢም ምክንያት ክልክል ይሆናሉ። ነገር ግን የወንድም የጡት እናት (ይህ ማለት የደም ወንድምህ የጡት እናት ላልጠባው ልጅ ጋብቻ አትከለከልም።) እና የራስ ልጅ የጡት እህት (የወለድከው ልጅ የጡት እህት ያንተ ሚስት አጥብታት የአንተ የጡት ልጅ እስካልሆነች ድረስ ለአንተ ጋብቻ አትከለከለም) አይከለከሉም።"

ትርጉሞችን አሳይ

58 ቋንቋ
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
FR Français الفرنسية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
HU Magyar المجرية
CS Čeština التشيكية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
AZ Azərbaycan الأذربيجانية
UZ O‘zbek الأوزبكية
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
BM Bambara البامبارية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية
DA Dansk الدنماركية
RN Kirundi الكيروندي
KMR Kurmancî الكرمنجية
MS Bahasa Melayu الملايو