+ -

عَنْ ‌أُبَيِّ بْنِ كَعْبٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«يَا أَبَا الْمُنْذِرِ، أَتَدْرِي أَيُّ آيَةٍ مِنْ كِتَابِ اللهِ مَعَكَ أَعْظَمُ؟» قَالَ: قُلْتُ: اللهُ وَرَسُولُهُ أَعْلَمُ. قَالَ: «يَا أَبَا الْمُنْذِرِ، أَتَدْرِي أَيُّ آيَةٍ مِنْ كِتَابِ اللهِ مَعَكَ أَعْظَمُ؟» قَالَ: قُلْتُ: {اللهُ لا إِلَهَ إِلا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ} [البقرة: 255]. قَالَ: فَضَرَبَ فِي صَدْرِي، وَقَالَ: «وَاللهِ لِيَهْنِكَ الْعِلْمُ، أَبَا الْمُنْذِرِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 810]
المزيــد ...

ኡበይ ቢን ከዕብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸው- እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ውስጥ ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አልኳቸው። " እርሳቸውም በድጋሚ "አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" አሉኝ። "{አላህ ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው።} [አልበቀራህ: 255]" (አያተል ኩርሲይ) አልኩኝ። እሳቸውም ደረቴን በመምታት "በአላህ እምላለሁ! እውቀት ያስደስትህ አቡ ሙንዚር!" አሉኝ።

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 810]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ኡበይ ቢን ከዕብን የአላህ መጽሐፍ ውስጥ ትልቁ አንቀፅ ማን ናት? በማለት ጠየቁት። መልስ ለመስጠት ካመነታ በኋላ አየቱል ኩርሲይ ናት {አላህ ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው።} በማለት መለሰ። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በዕውቀትና ጥበብ የተሞላ መሆኑን ለመጠቆም ደረቱን በመምታት በዚህ ዕውቀት እንዲደሰትና እንዲገራለት ዱዐ በማድረግ ትክክለኛ መልስ እንደመለሰ በመጥቀስ አበረታቱት።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht Azerisht الأوزبكية الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የኡበይ ቢን ከዕብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸው- ትልቅ ደረጃ፤
  2. አየቱል ኩርሲይ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ትልቋ አንቀፅ በመሆኗ መሸምደዱ፣ ትርጉሙን ማስተንተኑና እርሱን መተግበር ተገቢ ነው።