عن أَبِي أُمَامَةَ إِياسِ بنِ ثَعْلَبَةَ الحَارِثِيِّ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَنِ اقْتَطَعَ حَقَّ امْرِئٍ مُسْلِمٍ بِيَمِينِهِ، فَقَدْ أَوْجَبَ اللهُ لَهُ النَّارَ، وَحَرَّمَ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ» فَقَالَ لَهُ رَجُلٌ: وَإِنْ كَانَ شَيْئًا يَسِيرًا يَا رَسُولَ اللهِ؟ قَالَ: «وَإِنْ قَضِيبًا مِنْ أَرَاكٍ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 137]
المزيــد ...
ከአቡ ኡማማህ ኢያስ ቢን ሠዕለበህ አልሓሪሢይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
«"በመሃላው የሙስሊምን ሐቅ ያለአግባብ የወሰደ ሰው አላህ ለርሱ እሳትን ግድ አድርጎበታል፤ ጀነትንም በርሱ ላይ እርም አድርጓል።" አንድ ሰውዬም ለርሳቸው እንዲህ አለ፡ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! (የማለበት ጉዳይ) ትንሽም እንኳ ብትሆን (ይቀጣልን)?" እርሳቸውም "የአራክ እንጨት ቢሆን እንኳ! (ይቀጣበታል።)"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 137]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የሙስሊምን ሐቅ እያወቀ ያለአግባብ ለመውሰድ ዋሽቶ በአላህ ከመማል አስጠነቀቁ። የዚህ ተግባር ቅጣቱም እሳት መግባትና ጀነት መነፈግ ነው። ይህም ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው። አንድ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የተማለበት ነገር ትንሽ ብትሆን እንኳ?" አለ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "የወሰደው ለመፋቂያነት ከአራክ ዛፍ የሚወሰድ እንጨት እንኳ ብትሆን ይህን ቅጣት ይቀጣል።" አሉ።