+ -

عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المؤْمنينَ رَضيَ اللهُ عنها قَالَت:
دَخَلَتْ هِنْدٌ بِنْتُ عُتْبَةَ امْرَأَةُ أَبِي سُفْيَانَ عَلَى رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَتْ: يَا رَسُولَ اللهِ، إِنَّ أَبَا سُفْيَانَ رَجُلٌ شَحِيحٌ، لَا يُعْطِينِي مِنَ النَّفَقَةِ مَا يَكْفِينِي وَيَكْفِي بَنِيَّ إِلَّا مَا أَخَذْتُ مِنْ مَالِهِ بِغَيْرِ عِلْمِهِ، فَهَلْ عَلَيَّ فِي ذَلِكَ مِنْ جُنَاحٍ؟ فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «خُذِي مِنْ مَالِهِ بِالْمَعْرُوفِ مَا يَكْفِيكِ وَيَكْفِي بَنِيكِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1714]
المزيــد ...

ከአማኞች እናት ዓኢሻ ረዲየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች:
«የአቡ ሱፍያን ባለቤት የሆነችው ሂንድ ቢንት ዑትባ የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድ ገባችና እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አቡ ሱፍያን ንፉግ ሰው ነው። ሳያውቅብኝ ከገንዘቡ ካልወሰድኩ በቀር ለኔና ለልጆቼ የሚበቃንን ወጪ አይሰጠኝም። በዚህ እኔ ላይ ወንጀል ይኖርብኛልን?" የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ላንቺና ለልጆችሽ የሚበቃሽን ከገንዘቡ በአግባቡ ውሰጂ!" አሏት።»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1714]

ትንታኔ

ሂንድ ቢንት ዑትባ ረዲየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ስለባሏ አቡ ሱፍያን ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - ነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጠየቀች። እርሱ በገንዘቡ ስስታምና ንፉግ ነበር። እርሱ ሳያውቅ በድብቅ ከገንዘቡ ካልወሰደች በቀር ለርሷና ለልጆቿ የሚበቃትን ወጪ አይሰጣትም ነበር። ይህን በማድረጓ ወንጀል ይኖርባት እንደሁ ጠየቀች። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ባያውቅ እንኳ በተለምዶ በቂ ነው ተብሎ የተለመደውን ያህል ላንቺና ለልጆቹ ከገንዘቡ ውሰጂ።" አሏት።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ለሚስትና ለልጆች ወጪ ማውጣት ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  2. ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «ከገንዘቡ የሚበቃሽን ያህል በአግባቡ ውሰጂ!" በማለታቸው የተፈለገው: ወጪ ሸሪዓዊ ገደብ ስለሌለው ወደ ተለምዶ እያዞሩት ነው።»
  3. ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ፈትዋ ለመጠየቅ፣ ስሞታ ለማቅረብና ለመሳሰሉት ከሆነ አንድን ሰው በማያስደስተውም ነገር ማውሳቱ እንደሚፈቀድ ይህ ሐዲሥ ማስረጃ ነው። ይህ አይነት ክስተት ሐሜት ከሚፈቀድባቸው አጋጣሚዎች መካከል አንዱ ነው።"
  4. ቁርጡቢ እንዲህ ብለዋል: "ሂንድ አቡ ሱፍያንን በሁሉም ሁኔታዎቹ ስስታም አድርጋ አልገለፀችውም። እርሷ ከርሱ ጋር ያላትን ሁኔታ ነው የገለፀችው። እርሱ ለርሷና ለልጆቿ ይቋጥር ነበር። ይህ ማለት ግን ሙሉ ለሙሉ ንፉግ ነበር ማለትን አያሲዝም። ብዙ መሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲህ ያደርጋሉና። ለወዳጅነት ብለው ባዳዎችን ከቤተሰብ ያስቀድማሉ።"
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ