+ -

عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المؤْمنينَ رَضيَ اللهُ عنها قَالَت: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«تُقْطَعُ اليَدُ فِي رُبُعِ دِينَارٍ فَصَاعِدًا».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 6789]
المزيــد ...

ከአማኞች እናት ከዓኢሻህ (ረዲየሏሁ ዓንሃ) -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ:
"በሩብ ዲናርና ከዛ በላይ በሚያወጣ (ስርቆት) እጅ ይቆረጣል።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6789]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የአንድ ዲናር ሩብ እና ከዚህ በላይ የሚያወጣን ነገር የሰረቀ ሌባ እጁ እንደሚቆረጥ ገለፁ። ዋጋውም በንፁህ ወርቅ የ 1.06 ግራም ዋጋን ይመዝናል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ስርቆት ከትላልቅ ወንጀሎች የሚመደብ ነው።
  2. አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ የሌባን ቅጣት ወስኗል። እርሱም እጁን መቁረጥ ነው። አላህ እንዲህ እንዳለው {ሰራቂውንና ሰራቂይቱንም እጆቻቸውን ቁረጡ።} [አልማኢዳህ:38] የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሱናም የሚቆረጥበትን መስፈርቶች አብራርቷል።
  3. ሐዲሡ ውስጥ እጅ በማለት የተፈለገው መዳፍን ሲሆን በርሱና በክንዱ መካከል ከሚለየው አጥንት መቁረጥ ነው።
  4. የሌባን እጅ የመቁረጡ ጥበብ የሰዎችን ገንዘብ መጠበቅና ሌሎችን ወሰን አላፊዎች ማስጠንቀቅ ነው።
  5. ዲናር ማለት አንድ ሚሥቃል ወርቅ ነው። በዚህ ዘመንም በ24 ካራት ወርቅ (4.25 ግራም) ይመዝናል። የአንድ ዲናር ሩብም አንድ ግራም ከተወሰነ ሚሊ ግራም ይመዝናል።
ተጨማሪ