عَنْ أَنَسٍ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ:
مِنَ السُّنَّةِ إِذَا قَالَ الْمُؤَذِّنُ فِي أَذَانِ الْفَجْرِ حَيَّ عَلَى الْفَلَاحِ، قَالَ: الصَّلَاةُ خَيْرٌ مِنَ النَّوْمِ.
[صحيح] - [رواه ابن خزيمة والدارقطني والبيهقي] - [صحيح ابن خزيمة: 386]
المزيــد ...
ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«የፈጅር አዛን ላይ አዛን ባዩ "ሐይየ ዐለል ፈላሕ" ካለ በኋላ "አስሶላቱ ኸይሩን ሚነነውም" ማለቱ ከሱና ነው።»
[ሶሒሕ ነው።] - [Ibn Khuzaymah - Al-Bayhaqi - ዳረቁጥኒይ ዘግበውታል።]
አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተናገሩት ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ካፀደቁት ሱናዎች መካከል ሙአዚኑ የፈጅር አዛን ላይ ብቻ (ሐይየ ዓለል ፈላሕ) ካለ በኋላ (አስሶላቱ ኸይሩን ሚነነውም) ማለቱ ነው።