عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«أَكْثِرُوا ذِكْرَ هَادمِ اللَّذَّاتِ» يَعْنِي الْمَوْتَ.
[حسن] - [رواه الترمذي والنسائي وابن ماجه] - [سنن ابن ماجه: 4258]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልዕክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"ጥፍጥናን ቆራጩን ማስታወስ አብዙ።" ሞትን ማለታቸው ነው።
[ሐሰን ነው።] - - [ሱነን ኢብኑ ማጀህ - 4258]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የሰው ልጅ እርሱን ሲያስታውሰው የመጪው ዓለምን የሚያስታውስበትንና ለዱንያ ጥፍጥና በተለይ ደሞ ክልክል ለሆኑ መጣቀሚያዎች ያለውን ፍቅር ከቀልቡ የሚያጠፋለትን ሞትን አብዝቶ እንዲያስታውስ አነሳሱ።