1. ዋና ገጽ
  2. ምድቦች
  3. ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ሐዲሥ ሙስሊም የሆነ ሰው የሚናዘዘው ነገር ኑሮት ኑዛዜው እርሱ ዘንድ የተፃፈች ካልሆነች በቀር ሶስት ቀናቶችን ማደር አይገባውም።

عَنْ ابْنِ عُمَرَ رَضيَ اللهُ عنهُما أَنَّهُ سَمِعَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَا حَقُّ امْرِئٍ مُسْلِمٍ لَهُ شَيْءٌ يُوصِي فِيهِ، يَبِيتُ ثَلَاثَ لَيَالٍ، إِلَّا وَوَصِيَّتُهُ عِنْدَهُ مَكْتُوبَةٌ»، قَالَ عَبْدُ اللهِ بْنُ عُمَرَ رضي الله عنهما: «مَا مَرَّتْ عَلَيَّ لَيْلَةٌ مُنْذُ سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ ذَلِكَ إِلَّا وَعِنْدِي وَصِيَّتِي».

ከኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ ነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰማ:
"ሙስሊም የሆነ ሰው የሚናዘዘው ነገር ኑሮት ኑዛዜው እርሱ ዘንድ የተፃፈች ካልሆነች በቀር ሶስት ቀናቶችን ማደር አይገባውም።" ዐብደላህ ቢን ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ይህንን ሲናገሩ ከሰማው ጀምሮ ኑዛዜዬ እኔ ዘንድ የተፃፈች ሆና እንጂ አንድም ምሽት አላደርኩም።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 1627

ማብራሪያ

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሙስሊም የሆነ ሰው ትንሽ ብትሆን እንኳ አንዳች የሚናዘዘው ሐቅ ወይም ገንዘብ ኖሮ ኑዛዜው እርሱ ዘንድ የተፃፈች ካልሆነች በቀር ሶስት ቀናትን ማደር እንደማይገባው ተናገሩ። ዐብደላህ ቢን ዑመርም ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ: " የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ይህንን ሲናገሩ ከሰማው ጀምሮ ኑዛዜዬ እኔ ዘንድ የተፃፈች ሆና እንጂ አንድም ምሽት አድሬ አላውቅም።"

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. ኑዛዜ የተደነገገ መሆኑንና ኑዛዜውን ለማብራራት፣ የአላህን ትእዛዝ ለመተግበር፣ ለሞት ለመዘጋጀትና በሚያጠምደው ነገር ከመጠመዱ በፊት ኑዛዜውንና ኑዛዜው የሚውልበትን ቦታ እንዲያጤንበት መቻኮል እንደሚገባ እንረዳለን።
  2. ኑዛዜ ማለት ትርጉሙ: ቃል ኪዳን ማለት ነው። ይኸውም ሰውዬው ከሞተ በኋላ ለአንድ ግለሰብ የተወሰነውን የገንዘቡን ክፍል እንዲያንቀሳቅስ ቃል መግባት ወይም ለአንድ ግለሰብ ትናንሽ ልጆቹን እንዲከታተል ቃል ማስገባት ወይም ይቆጣጠረው የነበረን ማንኛውም ስራ ቁጥጥሩን ለሆነ ግለሰብ ቃል መግባት ማለት ነው።
  3. ኑዛዜ ሶስት ክፍሎች አሉት: 1- ተወዳጅ የሆነ ነው። እርሱም ከሞተ በኋላ ምንዳው እንዲደርሰው የተወሰነውን የገንዘቡን ክፍል በመልካምና በበጎ አድራጎት እንዲንቀሳቀስ መናዘዝ ነው። 2 - ግዴታ የሆነ ነው። እርሱም ያላወጣው ዘካ ወይም ከፋራና የመሳሰሉ በሸሪዓ መሰረት ግዴታ የሆኑበት የአላህም ሐቅ ሆነ ወይም እንደ እዳና አደራን መመለስ የመሰሉ የሰው ልጅም ሐቅ ቢሆን ያሉበትን ሐቆች መናዘዝ ነው። 3 - ክልክል የሆነ ነው። እርሱም ኑዛዜው ከገንዘቡ ከሲሶ ከፍ ካለ ወይም ለወራሽ የተናዘዘ ጊዜ ነው።
  4. የኢብኑ ዑመርን ረዲየሏሁ ዐንሁ ደረጃና መልካም ስራን ለመተግባርና የጥበበኛውን ፈጣሪ ድንጋጌ ለመከተል የነበረውን ፍጥነት እንረዳለን።
  5. ኢብኑ ደቂቅ አልዒድ እንዲህ ብለዋል: «ለሁለት ቀንና ሶስት ቀን ኑዛዜን ሳይፅፉ ማደር የተግራራው ችግርና ጭንቅን ለማስወገድ ሲባል ነው።»
  6. አንገብጋቢ ጉዳዮች በመፃፍ ሊጠበቁ ይገባል። ምክንያቱም መፃፍ ሐቆችን መጠበቂያና ማረጋገጫ ነውና።

ትርጉሞችን አሳይ

40 ቋንቋ
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية