+ -

عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«الدُّعَاءُ لاَ يُرَدُّ بَيْنَ الأَذَانِ وَالإِقَامَةِ».

[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي والنسائي] - [سنن الترمذي: 212]
المزيــد ...

ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"በአዛንና ኢቃም መካከል የሚባል ዱዓ አይመለስም (ተቀባይነቱ ጥርጥር የለውም)።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 212]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአዛንና ኢቃም መካከል የሚባል ዱዓ ያለውን ደረጃና እርሱ ለተቀባይነት የተገባና የማይመለስ ስለሆነ በዚህ ወቅት አላህን እንድንማፀን ገለፁ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية النيبالية الرومانية Oromisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ይህ ወቅት ዱዓ ለማድረግ ያለውን በላጭነት እንረዳለን።
  2. አንድ ዱዓ አድራጊ የዱዓን ስነስርዓቶች ካሟላ፣ ዱዓ ለማድረግ በላጩን ወቅትናና ስፍራ ካለመ፣ አላህን ከማመፅ ከራቀ፣ ነፍሱ አምታታችና አጠራጣሪ ነገር ውስጥ እንዳትገባ ከተጠነቀቀ፣ በአላህ ላይ ያለውን እሳቤ ካሳመረ በአላህ ፈቃድ ዱዓው ተቀባይነት ለማግኘት የተገባ ነው።
  3. ስለዱዓ ተቀባይነት ማግኘት መናዊ እንዲህ ብለዋል: «ማለትም የዱዓ መስፈርቶችን፣ ማዕዘናቶችንና ስነስርዓቶች ካሟላ በኋላ ከለመነው እንጂ ያጓደለው ነገር ካለ በመስተጓጎሉ ከነፍሱ በቀር ማንንም አይውቀስ።»
  4. የዱዓ ተቀባይነት ማግኘት: ወይ የለመነው በፍጥነት ትገኝለታለች ወይም በለመነው አምሳያ ጉዳት ዞር ይደረግለታል ወይም በመጪው አለም ለርሱ ድልብ ይደረግለታል። ይህም እንደአላህ ጥበብና እዝነት የሚወሰን ነው።