+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أُتِيَ بِلَحْمٍ فَرُفِعَ إِلَيْهِ الذِّرَاعُ، وَكَانَتْ تُعْجِبُهُ فَنَهَشَ مِنْهَا نَهْشَةً، ثُمَّ قَالَ:
«أَنَا سَيِّدُ النَّاسِ يَوْمَ القِيَامَةِ، وَهَلْ تَدْرُونَ مِمَّ ذَلِكَ؟ يَجْمَعُ اللَّهُ النَّاسَ الأَوَّلِينَ وَالآخِرِينَ فِي صَعِيدٍ وَاحِدٍ، يُسْمِعُهُمُ الدَّاعِي وَيَنْفُذُهُمُ البَصَرُ، وَتَدْنُو الشَّمْسُ، فَيَبْلُغُ النَّاسَ مِنَ الغَمِّ وَالكَرْبِ مَا لاَ يُطِيقُونَ وَلاَ يَحْتَمِلُونَ، فَيَقُولُ النَّاسُ: أَلاَ تَرَوْنَ مَا قَدْ بَلَغَكُمْ، أَلاَ تَنْظُرُونَ مَنْ يَشْفَعُ لَكُمْ إِلَى رَبِّكُمْ؟ فَيَقُولُ بَعْضُ النَّاسِ لِبَعْضٍ: عَلَيْكُمْ بِآدَمَ، فَيَأْتُونَ آدَمَ عَلَيْهِ السَّلاَمُ فَيَقُولُونَ لَهُ: أَنْتَ أَبُو البَشَرِ، خَلَقَكَ اللَّهُ بِيَدِهِ، وَنَفَخَ فِيكَ مِنْ رُوحِهِ، وَأَمَرَ المَلاَئِكَةَ فَسَجَدُوا لَكَ، اشْفَعْ لَنَا إِلَى رَبِّكَ، أَلاَ تَرَى إِلَى مَا نَحْنُ فِيهِ، أَلاَ تَرَى إِلَى مَا قَدْ بَلَغَنَا؟ فَيَقُولُ آدَمُ: إِنَّ رَبِّي قَدْ غَضِبَ اليَوْمَ غَضَبًا لَمْ يَغْضَبْ قَبْلَهُ مِثْلَهُ، وَلَنْ يَغْضَبَ بَعْدَهُ مِثْلَهُ، وَإِنَّهُ قَدْ نَهَانِي عَنِ الشَّجَرَةِ فَعَصَيْتُهُ، نَفْسِي نَفْسِي نَفْسِي، اذْهَبُوا إِلَى غَيْرِي، اذْهَبُوا إِلَى نُوحٍ، فَيَأْتُونَ نُوحًا فَيَقُولُونَ: يَا نُوحُ، إِنَّكَ أَنْتَ أَوَّلُ الرُّسُلِ إِلَى أَهْلِ الأَرْضِ، وَقَدْ سَمَّاكَ اللَّهُ عَبْدًا شَكُورًا، اشْفَعْ لَنَا إِلَى رَبِّكَ، أَلاَ تَرَى إِلَى مَا نَحْنُ فِيهِ؟ فَيَقُولُ: إِنَّ رَبِّي عَزَّ وَجَلَّ قَدْ غَضِبَ اليَوْمَ غَضَبًا لَمْ يَغْضَبْ قَبْلَهُ مِثْلَهُ، وَلَنْ يَغْضَبَ بَعْدَهُ مِثْلَهُ، وَإِنَّهُ قَدْ كَانَتْ لِي دَعْوَةٌ دَعَوْتُهَا عَلَى قَوْمِي، نَفْسِي نَفْسِي نَفْسِي، اذْهَبُوا إِلَى غَيْرِي، اذْهَبُوا إِلَى إِبْرَاهِيمَ، فَيَأْتُونَ إِبْرَاهِيمَ فَيَقُولُونَ: يَا إِبْرَاهِيمُ أَنْتَ نَبِيُّ اللَّهِ وَخَلِيلُهُ مِنْ أَهْلِ الأَرْضِ، اشْفَعْ لَنَا إِلَى رَبِّكَ أَلاَ تَرَى إِلَى مَا نَحْنُ فِيهِ، فَيَقُولُ لَهُمْ: إِنَّ رَبِّي قَدْ غَضِبَ اليَوْمَ غَضَبًا لَمْ يَغْضَبْ قَبْلَهُ مِثْلَهُ، وَلَنْ يَغْضَبَ بَعْدَهُ مِثْلَهُ، وَإِنِّي قَدْ كُنْتُ كَذَبْتُ ثَلاَثَ كَذِبَاتٍ، نَفْسِي نَفْسِي نَفْسِي، اذْهَبُوا إِلَى غَيْرِي، اذْهَبُوا إِلَى مُوسَى فَيَأْتُونَ، مُوسَى فَيَقُولُونَ: يَا مُوسَى أَنْتَ رَسُولُ اللَّهِ، فَضَّلَكَ اللَّهُ بِرِسَالَتِهِ وَبِكَلاَمِهِ عَلَى النَّاسِ، اشْفَعْ لَنَا إِلَى رَبِّكَ، أَلاَ تَرَى إِلَى مَا نَحْنُ فِيهِ؟ فَيَقُولُ: إِنَّ رَبِّي قَدْ غَضِبَ اليَوْمَ غَضَبًا لَمْ يَغْضَبْ قَبْلَهُ مِثْلَهُ، وَلَنْ يَغْضَبَ بَعْدَهُ مِثْلَهُ، وَإِنِّي قَدْ قَتَلْتُ نَفْسًا لَمْ أُومَرْ بِقَتْلِهَا، نَفْسِي نَفْسِي نَفْسِي، اذْهَبُوا إِلَى غَيْرِي، اذْهَبُوا إِلَى عِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ، فَيَأْتُونَ عِيسَى، فَيَقُولُونَ: يَا عِيسَى أَنْتَ رَسُولُ اللَّهِ، وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إِلَى مَرْيَمَ وَرُوحٌ مِنْهُ، وَكَلَّمْتَ النَّاسَ فِي المَهْدِ صَبِيًّا، اشْفَعْ لَنَا إِلَى رَبِّكَ أَلاَ تَرَى إِلَى مَا نَحْنُ فِيهِ؟ فَيَقُولُ عِيسَى: إِنَّ رَبِّي قَدْ غَضِبَ اليَوْمَ غَضَبًا لَمْ يَغْضَبْ قَبْلَهُ مِثْلَهُ قَطُّ، وَلَنْ يَغْضَبَ بَعْدَهُ مِثْلَهُ، وَلَمْ يَذْكُرْ ذَنْبًا، نَفْسِي نَفْسِي نَفْسِي اذْهَبُوا إِلَى غَيْرِي اذْهَبُوا إِلَى مُحَمَّدٍ، فَيَأْتُونَ مُحَمَّدًا فَيَقُولُونَ: يَا مُحَمَّدُ أَنْتَ رَسُولُ اللَّهِ وَخَاتِمُ الأَنْبِيَاءِ، وَقَدْ غَفَرَ اللَّهُ لَكَ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِكَ وَمَا تَأَخَّرَ، اشْفَعْ لَنَا إِلَى رَبِّكَ أَلاَ تَرَى إِلَى مَا نَحْنُ فِيهِ، فَأَنْطَلِقُ فَآتِي تَحْتَ العَرْشِ، فَأَقَعُ سَاجِدًا لِرَبِّي عَزَّ وَجَلَّ، ثُمَّ يَفْتَحُ اللَّهُ عَلَيَّ مِنْ مَحَامِدِهِ وَحُسْنِ الثَّنَاءِ عَلَيْهِ شَيْئًا، لَمْ يَفْتَحْهُ عَلَى أَحَدٍ قَبْلِي، ثُمَّ يُقَالُ: يَا مُحَمَّدُ ارْفَعْ رَأْسَكَ سَلْ تُعْطَهْ، وَاشْفَعْ تُشَفَّعْ فَأَرْفَعُ رَأْسِي، فَأَقُولُ: أُمَّتِي يَا رَبِّ، أُمَّتِي يَا رَبِّ، أُمَّتِي يَا رَبِّ، فَيُقَالُ: يَا مُحَمَّدُ أَدْخِلْ مِنْ أُمَّتِكَ مَنْ لاَ حِسَابَ عَلَيْهِمْ مِنَ البَابِ الأَيْمَنِ مِنْ أَبْوَابِ الجَنَّةِ، وَهُمْ شُرَكَاءُ النَّاسِ فِيمَا سِوَى ذَلِكَ مِنَ الأَبْوَابِ، ثُمَّ قَالَ: وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، إِنَّ مَا بَيْنَ المِصْرَاعَيْنِ مِنْ مَصَارِيعِ الجَنَّةِ، كَمَا بَيْنَ مَكَّةَ وَحِمْيَرَ -أَوْ كَمَا بَيْنَ مَكَّةَ وَبُصْرَى-».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 4712]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «ለአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ስጋ አመጡላቸው። ታፋውም ወደርሳቸው ቀረበ። ታፋ ያስደስታቸው ነበርና ከርሱ አንድ ጊዜ ከገመጡ በኃላ እንዲህ አሉ:
"እኔ የትንሳኤ ቀን የሰዎች አለቃ ነኝ። ይህ ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁን? አላህ የመጀመሪያውንም የመጨረሻውንም ሰዎች አንድ ሜዳ ላይ ይሰበስባል። (ከመጠቅጠቃቸውም የተነሳ) የአንድ ተጣሪ ድምፅ ያሰማቸዋልም፤ አንድ ሰው አዳርሶ መመልከትም ይችላል። ፀሐይም ወደነርሱ ትቀርባለች። ሰዎችም የማይችሉትና የማይቋቋሙት ችግርና ጭንቅ ይደርስባቸዋል። ሰዎችም "የደረሰባችሁን አትመለከቱምን? ለናንተ ወደ ጌታችሁ ሄዶ የሚያማልድን አትፈልጉምን?" ይላሉ። ከፊላቸው ለከፊላቸውም "እባካችሁ አደም ጋር ሂዱ!" ይላሉ። አደም ዐለይሂ ሰላም ዘንድ ይመጡና "አንተ የሰው ዘር አባት፤ አላህ በእጁ የፈጠረህ፤ ከፈጠራቸው ነፍሶች አንዱን ነፍስ በውስጥህ የነፋብህ፤ መላእክቶችን እንዲሰግዱልህ ያዘዘልህና የሰገዱልህ ነህ። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ምን ያህል (ችግር) እንደደረሰብን አትመለከትምን? ለኛ ጌታህ ዘንድ አማልድልን" ይላሉ። አደምም "ጌታዬ ዛሬ የተቆጣው ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ነው። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም። እኔን ከዛፏ ከለከለኝና አመፅኩት። ነፍሴ! ነፍሴ! ነፍሴ! ከኔ ውጪ ወደሌላ ሂዱ! እስኪ ወደ ኑሕ ሂዱ!" ይላቸዋል። ወደ ኑሕም በመሄድ "ኑሕ ሆይ! አንተ ወደ ምድር ነዋሪዎች የተላክ የመጀመሪያው መልክተኛ ነህ፣ አላህም አመስጋኙ ባሪያ ብሎ ጠርቶሃል። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ለኛ ጌታህ ዘንድ አማልድልን!" ይላሉ። ኑሕም "ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም። ለኔ የተሰጠችኝ አንድ ልመና ነበረች እርሷንም በህዝቦቼ ላይ አድርጌያታለሁ። ነፍሴ! ነፍሴ! ነፍሴ! ከኔ ውጪ ወደ ሌላ ሂዱ! እስኪ ወደ ኢብራሂም ሂዱ!" ይላቸዋል። ወደ ኢብራሂምም በመምጣት "ኢብራሂም ሆይ! አንተ የአላህ ነቢይና ከምድር ነዋሪዎች የአላህ ፍፁም ወዳጅ ነህ። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ለኛ ጌታህ ዘንድ አማልድልን!" ይላሉ። ኢብራሂምም "ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም። እኔ ሶስት ውሸቶችን ዋሽቼ ነበር። ነፍሴ! ነፍሴ! ነፍሴ! ከኔ ውጪ ወደሌላ ሂዱ! እስኪ ወደ ሙሳ ሂዱ!" ይላቸዋል። ወደ ሙሳም ይመጡና "ሙሳ ሆይ! አንተ የአላህ መልክተኛ ነህ፤ አላህ ከሰዎች ሁሉ መልዕክቱን በማሸከምና በማናገር የመረጠህ ነህ። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ለኛ ጌታህ ዘንድ አማልድልን!" ይላሉ። ሙሳም "ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም። እኔ መግደል ያልታዘዝኩትን ነፍስ ገድያለሁ። ነፍሴ! ነፍሴ! ነፍሴ! ከኔ ውጪ ወደሌላ ሂዱ! እስኪ ወደ ዒሳ ቢን መርየም ሂዱ!" ይላቸዋል። ወደ ዒሳም በመምጣት "ዒሳ ሆይ! አንተ የአላህ መልክተኛ ነህ፤ ወደ መርየም ባስተላለፋት ንግግር የተፈጠርክ፤ አላህ ከፈጠራቸው ነፍሶች መካከል አንዱ የሆንክ፤ በአንቀልባ ላይ ሆነህ ሰዎችን ያናገርክ ነህ። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ለኛ ጌታህ ዘንድ አማልድልን!" ይላሉ። ዒሳም "ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም። ስለዒሳ ምንም ወንጀል አልጠቀሰም። ነፍሴ! ነፍሴ! ነፍሴ! ከኔ ውጪ ወደሌላ ሂዱ! እስኪ ወደ ሙሐመድ ሂዱ!" ይላቸዋል። ወደ ሙሐመድም በመምጣት "ሙሐመድ ሆይ! አንተ የአላህ መልክተኛ ነህ፤ የነቢያት መደምደሚያ፤ አላህ ላንተ ያስቀደምከውንም ሆነ የሚመጣው ወንጀልህን ምሮሃል። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ለኛ ጌታህ ዘንድ አማልድልን!" ይላሉ። ወደ ዐርሽ ስር በመሄድም ለጌታዬ ሱጁድ አድርጌ እደፋለሁ። ከዚያም አላህ ከዛ በፊት ለአንድም ያልከፈተለትን የማመሰግንበትንና አሳምሬ የማወድስበትን አንዳች ቃላቶችን ይከፍትልኛል። ከዚያም "ሙሐመድ ሆይ! ራስህን ቀና አድርግ፤ ጠይቅ ይሰጥሃል፤ አማልድ ታማልዳለህ።" ይባላል። ራሴንም ቀና አደርግና "ጌታዬሆይ! ኡመቴ፤ ጌታዬ ሆይ! ኡመቴ፤ ጌታዬ ሆይ! ኡመቴ" እላለሁኝ። ለኔም "ሙሐመድ ሆይ! ከኡመትክ መካከል ሒሳብ (ምርመራ) የሌለባቸውን ከጀነት በሮች መካከል በቀኝ በር አስገባ። ከዛ ውጪ ባሉ በሮች ከሌሎች ሰዎች ጋር በጋራ ነው የሚገቡት።" እባላለሁኝ። ከዚያም እንዲህ አሉ "ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! በጀነት ሁለት መቃኖች መካከል ያለው ስፋት በመካና ሒምየር መካከል ያለውን ያህል ወይም ከመካ እስከ በስራ መካከል ያለውን ያህል ርቀት ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 4712]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በአንድ የምግብ ጥሪ ላይ ከባልደረቦቻቸው ጋር ሳሉ ለርሳቸው የበግ ታፋ ቀረበላቸው። እርሳቸው ዘንድ ከበግ ስጋ ተወዳጁም እርሱ ነበር። ከርሷም በጥርሳቸው ጫፍ አንድ ግዜ ገመጡና እንዲህ በማለት አናገሯቸው: እኔ የትንሳኤ ቀን የአደም ልጆች አለቃ ነኝ። ይህንንም ያሉት የአላህን ፀጋ ለመናገር ነው። ቀጥለው "ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁን? የትንሳኤ ቀን ሰዎች ሰፊና ለጥ ያለ ዝርግ መሬት ላይ ይሰበሰባሉ። በውስጧ የተሰበሰቡትንም አንድ ተጣሪ ያሰማቸዋል፤ መሬቷ ቀጥ ስላለች አንድም ሰው ከተመልካች መሸሸጊያ ስለሌለው ተመልካች ከነርሱ መካከል አንድም ሳይሰወርበት አጠቃልሎ ያያቸዋል። ማለትም አንድ ሰው ቢያወራ ሌላኛው ሰው ይሰማዋል፤ አይንም ይመለከታቸዋል ማለት ነው። ፀሐይም ወደ ፍጡራን የአንድ ማይል ያህል ትቀርባለች። የማይቋቋሙትና የማይችሉት ጭንቅና ችግር ያጋጥማቸዋል። በምልጃ ነፃ የሚወጡበትን መንገድ ይፈልጋሉ። አላህም ለኢማን ባለቤቶች ወደ ሰዎች አባት አደም ዘንድ እንዲመጡ ያሳውቃቸውና አላህ ዘንድ ለነርሱ እንዲያማልዳቸው በመከጀል ወደርሱ በመምጣት ደረጃውን ያወሳሉ። ለርሱም "አንተ አላህ በእጁ የፈጠረህ፤ መላዕክቱንም ያሰገደልህ፤ የሁሉንም ነገር ስሞች ያሳወቀህ፤ ከፈጠራቸው ነፍሶች መካከል አንዱን በውስጥህ የነፋብህ የሰው ዘር አባት አደም ነህ።" ይላሉ። እርሱም አለመቻሉን ለማሳወቅ "ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም።" በማለት ቀጥሎ ስህተቱን ይገልፅላቸዋል። እርሱም አላህ ዛፏን ከመብላት ከልክሎት መብላቱን ነው። ይልቁንም ነፍሴ ናት ምልጃ የሚገባት ይላቸዋል። ከኔ ውጪ ወደ ሌላ ሂዱ። ወደ ኑሕ ሂዱ ይላቸዋል። ወደ ኑሕም በመምጣት "አንተ የመጀመሪያ አላህ ወደ ምድር የላከው መልክተኛ ነህ። አላህም አመስጋኙ ባሪያ ብሎ ጠርቶሃል።" ይላሉ። ነገር ግን እርሱም እንደማይችል እንዲህ በማለት ያሳውቃቸዋል "ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም። ለኔ አንድ ዱዓ ነበረችኝ ህዝቦቼ ላይ አደረግኳት።" ይላል። ነፍሴ ናት ምልጃ የሚገባት ከኔ ውጪ ወደ ሌላ ሂዱ። ወደ ኢብራሂም ሂዱ ይላቸዋል። ወደ ኢብራሂምም በመምጣት "አንተ ምድር ውስጥ የአላህ ፍፁም ወዳጅ ነህ። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ጌታህ ዘንድ አማልድልን!" ይላሉ። እርሱም "ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም። እኔ ሶስት ውሸቶችን ዋሽቼያለሁ።" ይላቸዋል። ይህም ውሸት "አሞኛል" ማለቱ፣ "ይህ ታላቃቸው ነው የፈፀመው" ማለቱና ከንጉሱ ክፋት ለመዳን ለሚስቱ ሳራህ "እኔ ወንድምሽ እንደሆኑኩኝ ንገሪያቸው።" ማለቱን ነው። በእውነታው ስናየው እነዚህ ሶስት ቃላቶች ዘይቤያዊ ንግግሮች እንጂ ውሸት አይደሉም። ነገር ግን ይዘቷ የውሸት ይዘት ያላት ስለምትመስል ነፍሱን አሳንሶ ማማለድን ፈራ። አላህን እጅግ አዋቂ የሆነና ወደርሱ እጅግ ቅርብ የሆነ ሰው አላህን እጅግ በጣም ይፈራል። ስለዚህም ነፍሴ ናት ምልጃ የሚገባት። ከኔ ውጪ ወደ ሌላ ሂዱ ወደ ሙሳ ሂዱ ይላቸዋል። ወደ ሙሳ በመምጣትም "ሙሳ ሆይ! አንተ የአላህ መልክተኛ ነህ፤ አላህ ከሰዎች በተልእኮውና እርሱን በማናገር ያበለጠህ። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ጌታህ ዘንድ አማልደን።" ይላሉ። ሙሳም "ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም። እኔ በመግደል ያልታዘዝኩትን ነፍስ ገድያለሁ። ነፍሴ ናት ምልጃ የሚገባት። ከኔ ውጪ ወደሆነ ወደ ሌላ ሂዱ። ወደ ዒሳ ቢን መርየም ሂዱ።" ይላቸዋል። ወደ ዒሳም በመምጣት "ዒሳ ሆይ! አንተ የአላህ መልክተኛ ነህ፤ ወደ መርየም ባስተላለፋት ቃሉ የተፈጠርክና አላህ ከፈጠራቸው ነፍሶች መካከል አንዱ ነህ፤ በአንቀልባ ላይ ህፃን ሆነህ ሰዎችን አናግረሃል። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ጌታህ ዘንድ አማልደን።" ይላሉ። እርሱም "ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም። (ምንም ወንጀል ሳይጠቅስ ነፍሴ ናት ምልጃ የሚገባት። ከኔ ውጪ ወደ ሌላ ሂዱ። ወደ ሙሐመድ ሂዱ።" ይላቸዋል። ወደ ሙሐመድም በመምጣት "ሙሐመድ ሆይ! አንተ የአላህ መልክተኛ፤ የነቢያት መደምደሚያ፤ አላህ ላንተ ያሳለፈከውም ሆነ የሚመጣውን ወንጀል ምሮሃል። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ለኛ ጌታህ ዘንድ አማልድልን!" ይላሉ። እኔም ከዐርሽ ስር እመጣና ለጌታዬ ሱጁድ እደፋለሁ። ከዚያም አላህ ከዛ በፊት ለአንድም ያልከፈተለትን የማመሰግንበትንና አሳምሬ የማወድስበትን አንዳች ቃላቶችን ይከፍትልኛል። ከዚያም "ሙሐመድ ሆይ! ራስህን ቀና አድርግ፤ ጠይቅ ይሰጥሃል፤ አማልድ ታማልዳለህ።" ይባላል። ራሴንም ቀና አደርግና "ጌታዬ ሆይ! ኡመቴ፤ ጌታዬ ሆይ! ኡመቴ፤ ጌታዬ ሆይ! ኡመቴ" እላለሁኝ። ምልጃዬም ተቀባይነት ታገኛለች። ለርሳቸውም "ሙሐመድ ሆይ! ከኡመትክ መካከል ሒሳብ (ምርመራ) የሌለባቸውን ከጀነት በሮች መካከል በቀኙ በር አስገባ። ከዛ ውጪ ባሉ በሮች ከሌሎች ሰዎች ጋር በጋራ ነው የሚገቡት።" ይባላሉ። ቀጥለው እንዲህ አሉ "ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁኝ! የጀነት በሮች ዳርና ዳር ከመካ እስከ የመን ሰንዓ ድረስ ያለውን ይደርሳል። ወይም ከመካ እስከ ቡስራ ሻም መካከል ያለውን ይደርሳል።" ይህም የሐውራን ከተማ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ፈረንሳይኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الرومانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጥሪ አክባሪ መሆናቸውንና ከሁሉም ባልደረቦቻቸው ጋር አብረው ይበሉ እንደነበር እንረዳለን።
  2. ከሰው ዘር ባጠቃላይ ነቢያችን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በላጭ መሆናቸውን እንረዳለን።
  3. ቃዲ ዒያድ እንዲህ ብለዋል: "ሰይድ (አለቃ) ማለት ህዝቦቹን የሚመራና በጭንቅ ወቅት ወደርሱ የሚኬድ ማለት ነው ተብሏል። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በዱንያም ሆነ በመጪው ዓለም የሰው ዘር ሁሉ አለቃ ናቸው። ሐዲሡ ውስጥ የትንሳኤ ቀንን ብቻ የጠቀሱትም በዛ ወቅት የሚኖር አለቃነት ከፍ ያለ ስለሆነ፤ ሁሉም የርሳቸውን አለቃነትን ስለሚቀበልና አደምና ሁሉም ልጆቹ በርሳቸው አርማ ስር ስለሚሆኑ ነው።"
  4. አላህ አደምንና ቀጥለው የጠየቋቸውን ነቢያት እንዲጠይቁ የመራቸውና በቀጥታ ከጅምሩ ነቢያችንን ሙሐመድ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲጠይቁ ያልመራቸው ጥበቡ የነቢያችንን ደረጃ ይፋ ለማድረግ፤ እርሳቸው የደረጃ ከፍታና ወደ አላህ በተሟላ መልኩ በመቅረብ ጥግ ላይ የደረሱ መሆናቸውን ይፋ ለማድረግ ነው።
  5. አንድ ጉዳይ እንዲፈፀምለት የፈለገ ሰው የሚጠይቀውን አካል ከመጠየቁ በፊት እርሱን ባማሩ ባህሪያቱ መግለፅ በሸሪዓ የተደነገገ ነው። ይህም ጥያቄው ምላሽ እንዲያገኝ ስለሚያነሳሳ ነው።
  6. የማይችለውን ነገር የተጠየቀ ሰው ተቀባይነት ያለውን ምክንያት በማቅረብ አለመቻሉን ማሳወቅ ይፈቀድለታል። በጉዳዩ ላይ ይችላል ብሎ ያሰበውንም መጠቆሙ ይወደድለታል።
  7. በባሮች ላይ የትንሳኤ ቀን መቆም አስፈሪነቱና የመሰብሰብ ከባድነት መገለፁን እንረዳለን።
  8. ነቢያቶች ለዚህ ታላቅ ደረጃ አንገባም የሚለውን ለማሳወቅ ያለፈው ህይወታቸው እያስታወሱ መተናነሳቸው፤
  9. የትንሳኤ ቀን የሚከናወነውን ትልቁን ምልጃ ማፅደቅን እንረዳለን። እርሱም በፍጡራን መካከል ፍርድ እንዲሰጥ የሚደረግ ምልጃ ነው።
  10. ለአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ወሲላ" እና ምስጉኑን ስፍራ ማፅደቅን እንረዳለን።
  11. የአላህ መመስገኛ ቃላቶች አያልቁም። ስለዚህም በዚህ ስፍራ ላይ አላህ ለመልክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከዚህ በፊት ለማንም አሳውቆት የማያውቀውን ያማሩ ማወደሻ ቃላቶችን ያሳውቃቸዋል።
  12. የሙሐመድ ኡመት ምርጡ ኡመት መሆናቸውን፤ ከነርሱም መካከል ሒሳብ (ምርመራ) ሳይኖርባቸው ለብቻቸው የሚገቡበት የጀነት በር ያላቸው እንዳሉና በተቀሩት በሮችም ከሌላው ሰው ጋር በጋራ የሚገቡም እንዳሉ እንረዳለን።