عَنْ ‌عَائِشَةَ رضي الله عنها:
أَنَّ رَجُلًا قَعَدَ بَيْنَ يَدَيِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَقَالَ: يَا رَسُولَ اللهِ، إِنَّ لِي مَمْلُوكِينَ يَكْذِبُونَنِي وَيَخُونُونَنِي وَيَعْصُونَنِي، وَأَشْتُمُهُمْ وَأَضْرِبُهُمْ، فَكَيْفَ أَنَا مِنْهُمْ؟ قَالَ: «يُحْسَبُ مَا خَانُوكَ وَعَصَوْكَ وَكَذَّبُوكَ وَعِقَابُكَ إِيَّاهُمْ، فَإِنْ كَانَ عِقَابُكَ إِيَّاهُمْ بِقَدْرِ ذُنُوبِهِمْ كَانَ كَفَافًا، لَا لَكَ وَلَا عَلَيْكَ، وَإِنْ كَانَ عِقَابُكَ إِيَّاهُمْ دُونَ ذُنُوبِهِمْ كَانَ فَضْلًا لَكَ، وَإِنْ كَانَ عِقَابُكَ إِيَّاهُمْ فَوْقَ ذُنُوبِهِمُ اقْتُصَّ لَهُمْ مِنْكَ الْفَضْلُ»، قَالَ: فَتَنَحَّى الرَّجُلُ فَجَعَلَ يَبْكِي وَيَهْتِفُ، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «أَمَا تَقْرَأُ كِتَابَ اللهِ: {وَنَضَعُ الْمَوَازِينَ الْقِسْطَ لِيَوْمِ الْقِيَامَةِ فَلا تُظْلَمُ نَفْسٌ شَيْئًا}، الْآيَةَ»، فَقَالَ الرَّجُلُ: وَاللهِ يَا رَسُولَ اللهِ، مَا أَجِدُ لِي وَلهُمْ شَيْئًا خَيْرًا مِنْ مُفَارَقَتِهِمْ، أُشْهِدُكَ أَنَّهُمْ أَحْرَارٌ كُلُّهُمْ.

[ضعيف] - [رواه الترمذي]
المزيــد ...

ከምእመናን እናት ዓኢሻ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው፦
"አንድ ሰው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ፊት ለፊት በመቀመጥ እንዲህ አለ፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ሁለት ባሪያዎች አሉኝ። ይዋሹኛል፣ ያጭበረብሩኛል፣ ያምፁኛል እኔም እሰድባቸዋለሁም እመታቸዋለሁም በነሱ ላይ በምፈፅመው (ቅጣት) እንዴት ነው ሁኔታዬ?" እሳቸውም " ያጭበረበሩክ፣ ያመፁክና የዋሹክም መጠን የሚለካው በምትቀጣቸው መጠን ነው። የቀጣሀቸው በወንጀላቸው ልክ ከሆነ ስለሚመጣጠን (አላህ ዘንድ) ላንተም ለነሱም ሀቅ አይኖርም። ለወንጀላቸው ከሚገባው ቅጣት በታች ከቀጣሀቸው ላንተ ብልጫ አለህ። ለወንጀላቸው ከሚገባው ቅጣት በላይ ከቀጣሀቸው የጭማሪ ቅጣቷን ያህል ትቀጣለህ።" አሉት። "ሰውዬውም እያለቀሰና እየጮኸ አፈገፈገ።" የአላህ መልክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም " {በትንሳኤም ቀን ትክክለኛ ሚዛኖችን እናቆማለን። ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም።} የሚለውን አንቀፅ አታነብምን?" አሉት። ሰውዬውም "በአላህ እምላለሁ የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለኔም ሆነ ለነሱ ከመለያየት የተሻለ ምንም ነገር አላገኝም። እርሶ ምስክሬ ኖት ሁሉም ነፃ ወጥተዋል!" አላቸው።

Sahih/Authentic. - [At-Tirmidhi]

ትንታኔ

አንድ ሰውዬ ከባሮቹ ጋር ስላለው መስተጋብር ስሞታ ሊያቀርብ ወደነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን መጣ። ባሮቹ በሚያወሩት ይዋሹታል፣ በአደራዎች ይክዱታል፣ በስራቸው ያጭበረብሩታል፣ በትእዛዙ ያምፁታል። እሱም ስርአት ለማስያዝ ይሰድባቸዋልም ይመታቸዋልም። የትንሳኤ ቀን ከነርሱ ጋር ስለሚኖረው ሁኔታ ጠየቃቸው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን "ያጭበረበሩክ፣ ያመፁክና የዋሹክም መጠን የሚለካው በምትቀጣቸው መጠን ነው። የቅጣትህ መጠን ከወንጀላቸው ጋር እኩል ከሆነ ላንተም ለነሱም ምንም ሀቅ አይኖራችሁም፤ የቅጣትህ መጠን ከወንጀላቸው ካነሰ ላንተ የምንዳ ጭማሪና ደረጃ ይኖርሀል፤ የቀጣሀቸው ከወንጀላቸው በላይ ከሆነ ግን ትቀጣለህ፣ የተጨማሪ ቅጣትህ ያህልም ምንዳ ይወሰድና ለነሱ ይሰጣል አሉት። ሰውዬው ይህን ሲሰማ ድምፁን ከፍ አድርጎ እያለቀሰ አፈገፈገ። የአላህ መልክተኛም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን "የአላህን መጽሐፍ አታነብምን? {በትንሳኤም ቀን ትክክለኛ ሚዛኖችን እናቆማለን። ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም። (ሥራው) የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ቢሆንም እርሷን እናመጣታለን። ተቆጣጣሪዎችም በኛ በቃ።} [አልአንቢያእ: 47]" አሉት። የትንሳኤ ቀን አንድም ሰው አንዳችም አይበደልም። በሰዎች መካከል ፍትሀዊ ሚዛን ይሰፍናል። ሰውዬውም "በአላህ እምላለሁ የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለነሱም ሆነ ለኔ ከመተውና ከመለያየት የተሻለ ምንም ነገር አላገኝም። እርሶን ምስክሬ አደርጋለሁ! ሂሳብና ቅጣትን በመፍራት ሁሉንም ለአላህ ብዬ ነፃ ያወጣኋቸው ናቸው።" አለ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የአላህን ቅጣት በመፍራት ባሪያዎቹን ነፃ ማውጣቱ የሰሐቢዩን እውነተኝነት ያሳያል።
  2. ግፈኛን በግፉ ልክ የተመጣጠነ ወይም ከግፉ ያነሰ ቅጣት መቅጣት እንደሚፈቀድና ግፈኛው ከሰራው ግፍ በላይ ጨምሮ መቅጣት ግን ክልክል መሆኑን።
  3. ከሰራተኞችና ደካሞች ጋር በመልካም መስተጋብር መኗኗር እንደሚበረታታ ተምረናል።